ማይክሮሶፍት የየካቲት ወር ለዊንዶዉስ ምርቶቹ የደህንነት ማሻሻያ አቀረበ
ማይክሮሶፍት ኩባንያ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሳይበር ወንጀለኞች ጥቃት እየተፈጸመባቸው ያሉ ስድስት ቀደም ብለው ያልታወቁ አደገኛ የደህንነት ክፍተቶችን (Zero-day Vulnerabilities) ማግኘቱንና እነዚህን ክፍተቶች የሚደፍኑ የሶፍትዌር ማሻሻያዎችን #Updates) መልቀቁን አስታውቋል።
የመረጃ መንታፊዎች #Hackers የተጠቃሚዎችን ኮምፒውተር ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር፣ መረጃ ለመስረቅ ወይም ሲስተሞችን ለማቋረጥ የሚጠቀሙባቸው እነዚህ ክፍተቶች በሚከተሉት መንገዶች ሊከሰቱ ይችላሉ፦
1️⃣ ለማይክሮሶፍት ዎርድ #MS_Word ተጠቃሚዎች፦ አጠራጣሪ የሆኑ የዎርድ ፋይሎች በኢሜይል ወይም በቴሌግራም ሲላኩልዎ በፍጹም አይክፈቱ! አጥቂዎች ተጠቃሚው ፋይሉን ሲከፍት ብቻ ኮምፒውተሩን በቀጥታ እንዲቆጣጠሩ የሚያስችሉ ስልቶችን ጥቅም ላይ ማዋላቸው ተለይቷል።
2️⃣ አሳሳች ሊንኮች #Malicious_Links)፦ በዊንዶውስ ሲስተም ላይ ያሉ የደህንነት ማስጠንቀቂያዎችን ሰብረው የሚገቡ ሊንኮች ተገኝተዋል። ስለሆነም "ይህን ይጫኑ" የሚሉ አጠራጣሪ መልዕክቶችን ከመክፈት ይቆጠቡ።
3️⃣ ለባንክና ለንግድ ተቋማት፦ የኤስ.ኤ.ፒ (SAP) የንግድ ሶፍትዌር የምትጠቀሙ ተቋማት ፣ የደንበኞቻችሁ መረጃ ለጥቃት እንዳይጋለጥ በአስቸኳይ ሲስተሞቻችሁን እንድታዘምኑ (Update እንድታደርጉ) ይመከራል።
@reshadapp
@reshadapp

5February 11, 2026 750