የኔ እህት ብዙ ጊዜ የሰዉ ልጅ የራሱን ህይወት ከመምራት
ይልቅ የሰውን ህይወት መፈትፈት ይቀነዋል ።
ለእራሳቸዉ ህይወት መስጠት የነበረባቸዉን ጊዜ ነው
እንቺ ላይ እጣት እየቀሰሩ፣እየኮነኑሽ፣ እያንቋሸሹ በመኖር
ነው ጊዜያቸዉን የሚገሉት።
የኔ እህት አንቺም ከነዚህ ሰዎች ማንነት ተማሪ እንጂ
ሰዎችን ማንነት እንዳትላበሽና እንዳይኖር ተጠንቀቂ።
ይልቁንም፦
የሰዉ ህይወት ለመፈትፈት አትሞክሪ የአንቺን ህይወት
ለመፈትፈት እንዲሞክሩ ቦታ አትስጫቸዉ።
የሰውን ጉድለት ለመሙላት እንጂ ለማስፋት አትሩጪ
የአንቺንም ጉድለት ማንም እንዲያሰፋዉ አትፍቀጂ።
በንግግርሽ የሰዎችን ሞራል ዝቅ ለማረግ አትሞክሪ የሰዎች
ንግግር የአንቺን ሞራል እንዲያኮስ ቦታ አትስጪ።
ሰዎችን አትኮንኚ የሚኮንኑሽንም
ተያቸዉና ዝም ብለሽ ህይወትሽን ኑሪ።

7
3
1August 24, 2026 796 5