የእናቱን ወርቅ ሸጦ ልቦን ሰርጀሪ አሰርቶ ባሳከመው በዛው ልብ እኮ ነው ሌላ ያፈቀረችበት. 💔 ሰርጀሪ… — Pp of Pp ꨄ — TG.ME

የእናቱን ወርቅ ሸጦ  ልቦን ሰርጀሪ አሰርቶ
ባሳከመው  በዛው ልብ እኮ ነው  ሌላ ያፈቀረችበት. 💔


ሰርጀሪ ሲሰሯት የሌላ አረመኔ ሴት ልብ
ቀይረውባት እንጂ እሶ እንደዚህ አታረግም
ብሎ አስቦ ነበር ።


ግዜ ሲቆይ እውነቱን ሲረዳው ግን የመረረ ሳቅ ሳቅ መሀል ትርምስ ውስጥ ተንበርክኮ
መሪር ሳቁን ወደ ለቅሶ ቀስ ብሎ እየተቀየረ
ብዙ አነባ ።
ቡዙ ቀስት ጀርባው ላይ እንደተሰካ እና ደክሞት ሞቱን ብቻ
እንደሚናፍቀው ወታደር ጪላንጪል የምሬት ፈገግታ እና እንባው እንደዛ ወደቀ ።
አልተነሳም ቢነሳም በምን ወኔው
የእናቱን አይን ያያል ። እያንዳንዱ ከእጇ የጎረሰው እንጀራ አና ጉንጮ ላይ ያለው ማዲያት አንተ መፈሪያ ብለው የሚሳለቁበት ስለመሰለው ደፍሮ አይኗን አያይም ። ነግሬህ ነበር የሚለው
የፀፀት ጅራፍ ለመሸሽ ማንም ወደማያውቀው ሩቅ ወዳለች አኔዲት አሮጊት መነኩሼ ብቻ ወደሚኖሩበት ዛፍ
ወደበዛበት ሰፈር ተጠግቶ ለመነኩሴዋ እንጨት
እየፈለጠ ለፈለጠበት ቀዝቃዛ ውሀ
በንኬል እና ትኩስ እንጀራ በሚጥሚጣ ብቻ እየከፈሉት መኖር አማረው የት ነው ያለው
ይህ ቦታ እግሩ እንደመራው መሄድ ጀመረ
😭💔😓
💔19😭3❤1😇1
August 8, 2026 1.5K