#የአእላፋት_ዝማሬ ወዳንቺ የመጣው ወዳንቺ የመጣው በብሩህ ደመና ከሦስቱ አካል አንዱ ክርስቶስ ነውና የጠፋ በግ አዳም ታደሰ በጌታ ባንቺ ተፈጸመ የሰው ልጆች ደስታ #አዝ በደይን የተጣለች ሔዋን ተደሰተች የደስታ መፍለቂያ አንቺን ስላገኘች የበረከት ፍሬ ከአንቺ ተገኘልን የወይን ቦታ ነሽ ድንግል እናታችን #አዝ ወልድም ባሕርይሽን ባሕርይ አድርጎት ለፍጥረታት ጌታ መዓዛሽ ተስማምቶት ከአንቺ ይወለድ ዘንድ ፍጹም ሊላላክሽ በጥቂት አደገ ተልኮና ታዝዞሽ #አዝ ከድንግልና ጋር አንድ የሆነ ሐሊብ በሩካቤ ሳይሆን በብሥራት እንደ ንብ ከሆድ መጥበብ ጋር የመለኮት ስፋት አንቺ ሆነሽ ሳለ ታናሿ ሙሽሪት #አዝ በፍጡር ሕሊና የማይመረመር ዕጹብ ነው ድንቅ ነው የመፅነሷ ነገር እሳተ ነበልባል በሆድሽ ውስጥ ሲያድር ነደ ነበልባሉ አልፈጀሽም ነበር https://t.me/ortto
88
65December 30, 2023 59.9K 303