ለምን_ጠላኸኝ_ወንድሜ ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ የአንድ አባት ልጆችኮ ነን ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ የአንድ የእናት… — ኦርቶዶክሰ ተዋሕዶ መዝሙር/ortodoks tewahido mezmur — TG.ME

#ለምን_ጠላኸኝ_ወንድሜ ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ የአንድ አባት ልጆችኮ ነን ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ የአንድ የእናት ልጆችኮ ነን ብዙ ነዉ መንግስቱ አብረን እንወርሳለን ሰፊ ነው ግዛቱ አብረን እንወርሳለን የተካፈልኩትን ንብረት አጥፍቼ ብመለስ ዛሬ አባቴ ናፍቆኝ ብመጣ ልቤን አንገቴን ሰብሬ ለሁላችንም ይበቃል ብዙ ነው የርሱ መንግስት አይክፋህ እባክህ ወንድሜ ፍቅር ይበልጣል ከሃብት #አዝ ፊትህ በሐዘን አይጥቆር ድንጋዩን ጣለው ወንድሜ ተቅበዝባዥ እንዳያደርግህ እጅህ ቆሽሾ በደሜ ልብህን መልካም ብታደርግ ያንተም መስዋዕት ያርጋል ጌታ ለሁሉም እኩል ነው መታዘዝ ንጉሥ ያደርጋል #አዝ ብልጥ ስለሆንኩ አይደለም የተባረኩት በጌታ ጽኑ መሻቴን አይቶ ነው በኩር ያደረገኝ ስመታ የበቀል ጦርክን ሸሽቼ በባዕድ አገር ብኖርም በልጅ በትዳር ባርኮኛል አብረን እንኑር በሰላም #አዝ ብልጥ ስለሆንኩ አይደለም የተባረኩት በጌታ ጽኑ መሻቴን አይቶ ነዉ በኩር ያደረገኝ ስመታ የበቀል ጦርክን ሸሽቼ በባዕድ ሀገር ብኖርም በልጅ በትዳር ባርኮኛል አብረን እንኑር በሰላም ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ http://T.me/ortto

👍59❤57
March 12, 2023 45.8K 310