በጎል_በጎል በጎል በጎል ሰብአ ሰገል /4/ በጎል ሰብአ ሰገል ሰገዱለት /4/ ፀሐይ /2/ ፀሐይ ሰረቀ /2/… — ኦርቶዶክሰ ተዋሕዶ መዝሙር/ortodoks tewahido mezmur — TG.ME

#በጎል_በጎል በጎል በጎል ሰብአ ሰገል /4/ በጎል ሰብአ ሰገል ሰገዱለት /4/ ፀሐይ /2/ ፀሐይ ሰረቀ /2/ ፀሐይ ሰረቀ ክርስቶስ ተጠምቀ /4/ #አዝ አንቺ ዮርዳኖስ ምንኛ ታደልሽ /2/ የእግዚአብሔር መንፈስ ከላይ ወርዶብሽ የዓለም መድኃኒት ተጠመቀብሽ /2/ #አዝ ድንግል ማርያም ንፅህት ቅድስት /2/ የጌታዬ እናት ምስጋና ይገባሻል ከሴቶች ሁሉ አንቺን መርጦሻል /2/ #አዝ አዲስ ሙሽራ ሲመጣ እያያችሁ/2/ የዮርዳኖስ ወንዞች ስለምን ሸሻችሁ/2/ #አዝ እናንት ተራሮች እግር ሳይኖራቹ/2/ እንዴት እንደ ጊደር ሽቅብ ዘለላችሁ/2/ #አዝ ድንግል ማርያም ያስገኘሽው ፍሬ/2/ ሕዝቦቹን ለማዳን ተወለደ ዛሬ ሕዝቦቹን ለማዳን ተጠመቀ ዛሬ /2/ #አዝ እልል እልል ደስ ይበለን /2/ ወልድ ተወልዶ ነጻ ወጣን ዮሐንስ አጥምቆ ድል አገኘን /2/ http://T.me/ortto

👍47❤37
January 18, 2023 41.7K 154