አእላፋት ዝማሬ 2018 አይኖቼ ማዳኑን አይተዋልና ዓይኖቼ ማዳኑን አይተዋልና /2/ ይገባዋል /2/ ክብርና… — ኦርቶዶክሰ ተዋሕዶ መዝሙር/ortodoks tewahido mezmur — TG.ME

#አእላፋት ዝማሬ 2018 አይኖቼ ማዳኑን አይተዋልና ዓይኖቼ ማዳኑን አይተዋልና /2/ ይገባዋል /2/ ክብርና ምስጋና #አዝ ከሰማይ ወረደ ሰውን በማፍቀር ኃያሉ ጌታችን ቸሩ እግዚአብሔርበቤተልሔም ዋሻ በዚያ በግርግም ተወለደ ዛሬ መድኀኔዓለም #አዝ የተነበዩለት ብዙ ነቢያት ከድንግል ተወልዶ አዳነን በእውነት ከበደል ጉራንጉር አነሣን ከትቢያ በአንድነት እንዘምር እንበል ሃሌሉያ #አዝ የተናቅን ስንሆን እኛን ሊያከብር ወድዶ በፍቅር አከበረን ራሱን አዋርዶ ምን ዓይነት ፍቅር ነው ፍጹም ምሕረት የአምላክ መወለድ በከብቶች በረት #አዝ በንጽሕና ጸንተሽ ቤተ መቅደስ የኖርሽ በሕቱም ድንግልና መድኀኒትን ወስድሽ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ ጌታ ተወልዷል ከድንግል የሰዎች አለኝታ https://t.me/ortto

❤24
December 8, 2025 13.3K 40