አእላፋት ዝማሬ 2018 መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው አማኑኤል የለም የሚሳነው… — ኦርቶዶክሰ ተዋሕዶ መዝሙር/ortodoks tewahido mezmur — TG.ME

#አእላፋት ዝማሬ 2018 መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው አማኑኤል የለም የሚሳነው እርሱ ቃል ሲናገር ተራራው ሜዳ ነው መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው #አዝ አላስብም አልፈዋለሁ ብዬ ጉንጭ አልፎ ትራሴን እያጠበ እንባዬን እየተፈጸመ ኃይሉ በድካሜ ማእበሉን አለፍኩኝ ቀለለልኝ ሸክሜ #አዝ የቤቴ እራስ ነው የእቅዴ መሪ በክፉም በደጉም ነፍሴን አስተማሪ ፈጥሮ የማይረሳኝ ቤዛዬ ደረሰ ቤቴን ደስታ ሞላው እንባዬ ታበሰ #አዝ ትናንት ባዶ ነበር የለኝ የሚሰፈር አንዳች አልነበረኝ የሚታይ የሚቆጠር ከርሱ የተነሳ ዛሬ ግን ሙሉ ነኝ ክብር ለእርሱ ይሁን አለ የማይተወኝ #አዝ እየከለከለ ለእኔ የማየጠቀመኝን በጊዜ እየሰጠ ደግሞ የሚረባኝን ሁሉ በእርሱ ሆኗል አልሆነም ያለ እርሱ ውዳሴ ምስጋና ይድረስ ለንጉሱ https://t.me/ortto

❤41👍3
December 7, 2025 11.7K 84