One Love School Official: post #3271 — TG.ME

ለክቡራን የOne Love School እና Pent School ወላጆች
ውድ ወላጆቻችን፣
በመጀመሪያ ለትምህርት ቤታችን ላሳያችሁት እምነት፣ ድጋፍና ትብብር ከልብ እናመሰግናለን። የልጆቻችሁ ትምህርት ለእኛ ሁልጊዜም ዋነኛ ቅድሚያችን ነው።
እንደምታውቁት፣ One Love School (1–8) በቤት ኪራይ ሁኔታ ምክንያት በአሁኑ ቦታ ሥራውን መቀጠል አልቻለም። ሆኖም ይህ ማለት የትምህርት አገልግሎታችን ተቋርጧል ማለት አይደለም። ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በPent School ስም በተሻለ አቅም፣ በተሻለ አደረጃጀት እና በጠንካራ ራዕይ ሥራችንን እንቀጥላለን።
በትምህርት መመሪያው መሠረት የትምህርት ቤት መዘጋትም ሆነ መከፈት ከአዲሱ የትምህርት ዘመን 2 ወይም 3 ወራት በፊት ለወላጆች ማሳወቅ ይገባል። በመሆኑም ይህን ማስታወቂያ አሁን በመስጠታችን ለልጆቻችሁ የሚሻለውን ውሳኔ ለመወሰን በቂ ጊዜ እንዲኖራችሁ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ፣ በመረጃ ብቻ እንዳትወስኑ እንጠይቃለን። ወደ ትምህርት ቤቱ በአካል ይምጡ፤ እየተከናወኑ ያሉትን የግንባታ፣ የማሻሻያ እና የአደረጃጀት ሥራዎች በዓይናችሁ ይመልከቱ፤ ከአስተዳደሩ ጋር ተወያዩ፤ የምታቀርቡትን ሀሳብ እና ጥቆማ ያካፍሉን። ገንቢ ሀሳቦቻችሁን አቅማችን በፈቀደ መጠን ለመተግበር ዝግጁ ነን።
Pent School ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ተግባር ገብቷል። በትምህርት ጥራት፣ በዲሲፕሊን፣ በእንግሊዝኛ ትምህርት፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመማሪያ ሥርዓት፣ በትራንስፖርት አገልግሎት እና በዘመናዊ የመማሪያ አካባቢ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ሙሉ ዝግጅት ተደርጓል።
ውድ ወላጆች፣ በዚህ የሽግግር ሂደት በቅርብ መከታተላችሁ፣ ጥያቄ መጠየቃችሁ እና ሀሳብ መስጠታችሁ የልጆቻችሁን የወደፊት ስኬት በጋራ ለመገንባት ያላችሁን ቁርጠኝነት ያሳያል። ስለዚህ ይህን ትብብር በቀጣይም እንዲቀጥል በአክብሮት እንጋብዛችኋለን።
"One Love ታሪኩን በክብር አጠናቋል፤ Pent School ደግሞ የተሻለ የወደፊት ጉዞን በቁርጠኝነት ጀምሯል። ይህን አዲስ ጉዞ ከእናንተ ጋር በመሆን ለልጆቻችን የተሻለ ዕድል እንፈጥራለን።"
ከአክብሮት ጋር፣
ውቢሸት ግርማው ዳኘው
ባለቤትና መስራች
Pent School / One Love KG
❤33🫡9👏7
July 10, 2026 2.8K 5