MoH ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የሙያ ፈቃድ የፅሑፍ ፈተና የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ሙያ ተመዛኞች፣… — 🦋Exit Exam( የመውጫ ፈተና) — TG.ME

#MoH ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የሙያ ፈቃድ የፅሑፍ ፈተና የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ሙያ ተመዛኞች፣ ውጤታችሁን ከነገ ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም ጀምሮ መመልከት የምትችሉ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል። የፅሑፍ ፈተናውን ያለፋችሁ ተመዛኞች የተግባር ፈተና ለመውሰድ ነሐሴ 23 እና 24/2018 ዓ.ም ብቻ ምዝገባ የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል። በመሆኑም በተገለፁት ቀናት https://hple.moh.gov.et/ ላይ በመግባት የብሔራዊ መለያ ቁጥር (FAN) እና Password በማስገባት መፈተኛ ጣቢያ በመምረጥ ምዝገባችሁን እንድታከናውኑ ተብሏል። ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ ሲስተሙ የሚሰጣችሁን QR Code የያዘ ስሊፕ ይዛችሁ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡ ✤Join us https://t.me/mock_news https://t.me/mock_news

❤5
August 27, 2026 773 3