የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ምን አሉ ? (የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት መግለጫ) - የዘንድሮው ውጤት ከአምናው በጥሩ ደረጃ ተሻሽሏል። - ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርስቲ አስገብቶ ማስፈተን በተጀመረበት የመጀመሪያ አመት ያለፉ 3.2% ፣ በሁለተኛው 2.9% ፣ በሶስተኛው 5.2% ፣ በአምናው አራተኛው ዓመት 8.9% ደረሰ አሁን በአምስተኛው ዓመት 12.8% ነው ያለፉት። - ዘንድሮ በ2018 ብሔራዊ ፈተና የተመዘገበው ተማሪ ቁጥር 563,960 ሲሆን 550,210 ተማሪ ነው የተፈተነው። - ፈተናውን ያለፈው ተማሪ ብዛት 70,544 ነው። - ከተፈጥሮ ሳይንስ 16.6% አልፈዋል። ከማህበራዊ ሳንይስ 8.3% አልፈዋል። #በፐርሰንት - ክልሎች ካስፈተኗቸው ተማሪዎች ምን ያህል ተማሪ አሳለፉ ? (ያሰፈተኗቸው ተማሪዎች ቁጥር ይለያያል) 1. አዲስ አበባ 32.3% 2. ሀረሪ 22.67% 3. አፋር 15.6% 4. አማራ 15.56% 5. ድሬዳዋ 11.29% 6. ትግራይ 11.2% 7. ኦሮሚያ 10.53% 8. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 9.23% 9. ሶማሌ 9.2% 10. ሲዳማ 6.95% 11. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 6.12% 12. ደቡብ ኢትዮጵያ 5.82% 13. ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 4.92% 14. ጋምቤላ 3.74% በቁጥር ምን ያህል ተማሪ ከየክልሉ አለፉ ? (ያስፈተኑት ቁጥር ይለያያል) 1. ኦሮሚያ ➡ 20,807 ተማሪዎች 2. አዲስ አበባ ➡ 18,646 ተማሪዎች 3. አማራ ➡ 15,225 ተማሪዎች 4. ትግራይ ➡ 3,146 ተማሪዎች 5. ደቡብ ኢትዮጵያ ➡ 3,011 ተማሪዎች 6. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ➡ 2,800 ተማሪዎች 7. ሲዳማ ➡ 1,827 ተማሪዎች 8. ሶማሌ ➡ 1,616 ተማሪዎች 9. ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ➡ 835 ተማሪዎች 10. አፋር ➡ 705 ተማሪዎች 11. ሀረሪ ➡ 599 ተማሪዎች 12. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ➡ 457 ተማሪዎች 13. ድሬዳዋ ➡ 410 ተማሪዎች 14. ጋምቤላ ➡ 280 ተማሪዎች - ባለፈው ዓመት ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች 1,232 ነበሩ ዘንድሮ ምንም ተማሪ ያላሳለፉ 565 ናቸው። - ከዚህ ቀደም ምንም ተማሪ ካላሳለፉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በኮፒዩተር ፈተና ወደ 4,500 ተማሪዎች አልፈዋል። ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች በክልል ምን ያህል ናቸው ? • ኦሮሚያ 156 • አማራ 98 • ደቡብ ኢትዮጵያ 86 • ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 69 • ትግራይ 48 • ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 29 • ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 22 • አፋር 21 • ሲዳማ 16 • ሶማሌ 9 • ድሬዳዋ 5 • ሀረሪ 3 • ጋምቤላ 2 • አዲስ አበባ 1 - ሁሉንም ያስፈተኑትን ተማሪዎች ያሳለፉ 100% ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች ባለፈው አመት 62 ነበሩ ዘንድሮ 88 ሆነዋል። በክልሎች ምንም ያህል ትምህርት ቤቶች 100% አሳለፉ ? • ኦሮሚያ 37 • አዲስ አበባ 24 • አማራ 8 • ደቡብ ኢትዮጵያ 4 • ትግራይ 4 • ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 3 • ሲዳማ 2 • አፋር 1 • ድሬዳዋ 1 • ሀረሪ 1 • ሶማሌ 1 • ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 1 - በኮምፕዩተር እና በወረቀት በተፈተኑ ተማሪዎች መካከል ያለው የማለፍ ምጣኔ ትልቅ ልዩነት አለው። ኦንላይ የተፈተኑ 18.3% አልፈዋል። በወረቀት የወሰዱ 4.2% ናቸው ያለፉት። አንዱ ቶሎ በወረቀት ከመፈተን መውጥቶ ኦላይን ለመስጠት እቅድ አለው 60% ነው ዘንድሮ ቀጣይ አመት 100% ኦንላይን ሁሉንም። - የዘንድሮው ከፍተኛ ውጤት ስንት ነው ? • በተፈጥሮ ሳይንስ • 🥇 ከወንድ 👉 591/600 ኦዳ ስፔሻል ቦርንዲግ ትምህርት ቤት አዳማ 🥇 ከሴት 👉 583/600 ከአገው ምድር ትምህርት ቤት እንጅባራ • በማህበራዊ ሳንይንስ • 🥇 ከወንድ 👉 576/600 ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት 🥇 ከሴት 👉 569/600 አዲስ አበባ ቦሌ ሱፐርሆሊሴቪየር ትምህርት ቤት - ስልክ ይዘው የገቡ 265 ተማሪዎች ከፈተናው ተሰርዘዋል። - ኮምፒዩተር ላይ ባለ " ኢሬጉላተሪ " ተብለው ጉዳያቸው እየተጣራ ያለ አለ። - ከዚህ በፊት ከነበረው መሻሻል እየታየ ስለሆነ በጣም ደስተኞች ነን። - ዘንድሮም ወደ ሬሜዲያል የሚገቡ ተማሪዎች ይኖራሉ። - ሬሜዲያል ሁሌ የሚኖር አይደለም። በሚያልፈው ተማሪ ብዛት ነው የሚወሰነው። ዘንድሮ 70 ሺህ ተማሪ ስላለፈ ዘንድሮ ሬሜዲያል የሚገባው ይቀንሳል። 📌 ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ሰኞ ወይም ከነገ ወዲያ ማክሰኞ ጀምሮ ውጤታቸው ማየት ይችላሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተማሪዎች ውጤት የሚመለከቱባቸውን አማራጮች ተከታትሎ ያቀርባል። Join us https://t.me/mock_news https://t.me/mock_news
TelegramExit news| $fx 👁️🔹This channel is created to Mastering money through knowledge. Forex • Crypto • Wealth Education 📈 for more info & ad's DM @Zedreamer ☢️ 🧑💼
6
2