የቀድሞ የቼልሲ የግሎባል ኮመርሻል እንቅስቃሴዎች ሃላፊ ክርስቲያን ፐርስሎው ኤንዞ ፈርናንዴዝ በ £125m ወደ… — Ethio_Chelsea FC News — TG.ME

🗣 የቀድሞ የቼልሲ የግሎባል ኮመርሻል እንቅስቃሴዎች ሃላፊ ክርስቲያን ፐርስሎው ኤንዞ ፈርናንዴዝ በ £125m ወደ ማንቼስተር ሲቲ ስለመዛወሩ የሰጠው አስተያየት፡

"ቼልሲ ሲቲዎች ያቀረቡትን የገንዘብ መጠን ካላገኙ ኤንዞን በደስታ በክለቡ እንደሚያስቀሩት አስተሳሰብ በማንቼስተር ሲቲ አእምሮ ውስጥ መትከል ነበረባቸው፤ ሲቲዎችም ይህንን ያመኑት ይመስለኛል። እናም የቀረበው ገንዘብ ወደፈለጉት መጠን ባይቀርብ ኖሮ ኤንዞን ያስቀሩት ነበር ብዬ አስባለሁ። ይህ በቼልሲ እግር ኳስ ክለብ በኩል የተደረገ እጅግ በጣም ምርጥ የሆነ የንግድ/የሽያጭ ችሎታ ማሳያ ነው።"

"እሱና ኩኩሬላ ባለፈው የውድድር ዘመን ማጠቃለያ ላይ የአመራሩን አካል የነቀፉበት/የተቹበት ቀን፣ እነዚያ ሁለት ተጫዋቾች ከክለቡ የሚለቁበት ቀን እንደሚሆን አውቄ ነበር። በቼልሲ ውስጥ መሰል ባህሪ ያሳየ ማንኛውም ሰው አሰልጣኞችን ጨምሮ በሩ ተከፍቶለት ከክለቡ ተሸኝቷል።
👍11❤5
September 5, 2026 949