የጥንቃቄ መልዕክት ;10/7/2018 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን… — Ethio Education (ትምህርት), Iphone Novel Jobs,School,Books,Engineerings,Accounting,Economics,Scholarship,Maths,Health,ICT — TG.ME

የጥንቃቄ መልዕክት ;10/7/2018 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የህብረተሰቡን ጤና ለማስጠበቅ እና ህገ ወጥነትን ለመከላከል በሚያደርገው የቁጥጥር ስራ ህገወጥ፣ ምንጩ ያልታወቀና ጥራት የጎደለው ሔራል የገበታ ጨዉ የተሰኘ ምርት አግኝቷል። በቁጥጥር ወቅት የተገኝው ሔራል የገበታ ጨዉ ምርቱ በላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ የአይወዲን ይዘቱ ከደረጃ በታች የሆነ ፣የምርት መያዣ ከረጢቱ ደረጃዉን ያልጠበቀ እና ታሽጎ ለገበያ የቀረበዉ ምርት የንፅህና ጉድለት እና ባዕድ ነገር ያለበት መሆኑ ተደርሶበታል። በተጨማሪም ድርጅቱ ሔራል የገበታ ጨዉ በሚል ስያሜ ከአዲስ አበባ ምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን የጤና ብቃት ማረጋገጫ ሳያወጣ የብቃት ማረጋገጫ እንዳወጣ በማስመሰል እና የጨዉ መያዣ ከረጢቱ ላይ ባልተገባ መልኩ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ስም በመጥቀስ ተጠቃሚዉን ማህበረሰብ በማጭበርበር በገበያ ላይ ምርቱ የተሰራጨ መሆኑ ተደርሶበታል፡፡ በመሆኑም ባለስልጣኑ በገበያ ላይ የተሰራጨው የጨው ምርት የጤና ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል ህብረተሰቡ እንዳይጠቀመው መልዕክት እያስተላለፈ የተጠቀሰው የጨው ምርት የሚመለከተው አካል እንዲሰበስበው ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም ባለስልጣኑ በተሰጠው ስልጣን እና ኃላፊነት መሰረት ድርጁቱ የብቃት ማረጋገጫ ሳያወጣ በህገወጥ መንገድ ምርቱ በገበያ ላይ በማዋል ፣ ከደረጃ በታች የሆነ ምርት ለህብረተሰቡ በማቅረብ ፣የባለስልጣን መስሪያቤቱን ስም በህገወጥ ምርት ህጋዊ አስመስሎ በመጠቀም እና የንፅህና ጉድለት እና ባዕድ ነገር ያለበት ምርት ለገበያ በማቅረቡ ምርቱ ከገበያ እንዲሰበሰብ ማህበረሰቡም እንዳይጠቀም እንዲሁም አምራች ድርጅቱ በህግ እንዲጠየቅ አድርጓል፡፡

March 19, 2026 238 1