AAU #UAT በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም በመደበኛ መርሐግብር የቅድመ-ምረቃ ትምህርት ለመከታተል… — Info — TG.ME

#AAU #UAT

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም በመደበኛ መርሐግብር የቅድመ-ምረቃ ትምህርት ለመከታተል ላመለከታችሁ የቅድመ-ምረቃ የመግቢያ ፈተና (UAT) ጳጉሜን 02 እና 03/2018 ዓ.ም ይሰጣል።

ፈተናው በተጠቀሱት ቀናት በሦስት ፈረቃ ማለትም ፈረቃ 1: ጠዋት ከ2:30-5:00 ፈረቃ 2: ረፋድ ከ5:30-8:00 ፈረቃ 3: ከሰዓት ከ8:30-11:00 የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

መርሐግብሩን እዚህ በጥንቃቄ ይመልከቱ። የመፈተኛ ማዕከልዎን የመፈተኛ ሰዓትዎን በደንብ ይመልከቱ።

🔔 ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ፣ የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ እና ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲን ለፈተና ማዕከልነት የመረጣችሁ አመልካቾች ወደ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል የተዘዋወራችሁ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ለፈተና ማዕከል የመረጡ ማየት የተሳናቸው አመልካቾችች በሙሉ ዋናው ግቢ በሚገኘው የአካል ጉዳተኞች ማዕከል ላብ 1 ማክሰኞ ጳጉሜን 03/2018 ዓ.ም በፈረቃ 3 ፈተናቸውን የሚወስዱ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር 💠

🔴ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ!

✈️
https://t.me/Tmhrt_Minister
✈️
https://t.me/Tmhrt_Minister
❤2
September 5, 2026 1.9K 4