አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ! 🚨
ሰሞኑን በቴሌግራም ላይ እጅግ አደገኛ የሆነ የአካውንት ጠለፋ እና የማጭበርበር ድርጊት እየተፈጸመ ይገኛል።
በጣም ፀያፍ የሆኑ ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን እንደ ሽፋን በመጠቀም፣ ከስራቸው ሊንክ (Link) ያያይዛሉ።ሊንኩ የሚላክላችሁ ከማታውቁት ሰው ብቻ ሳይሆን፣ አካውንታቸው በተጠለፈ የቅርብ ጓደኞቻችሁ ወይም ዘመዶቻችሁ ስም ሊሆን ይችላል።
ከዚያ ሊንኩን ልክ እንደነካችሁት የእናንተም የቴሌግራም አካውንት ወዲያውኑ በሰከንዶች ውስጥ ይጠቃል፣ ከቁጥጥራችሁ ውጪ ይሆናል። ከዚያም በእናንተ ስም ለሌሎች ሰዎች ተመሳሳይ ቫይረስ ይልካል።
⚠️ስለዚህ ከማንኛውም ሰው (የምታውቁትም ይሁን የማታውቁት) የሚላክላችሁን ማናቸውንም አይነት ሊንክ በፍጹም አትንኩ! አትክፈቱ!
እባካችሁ ይህንን መረጃ ለምትወዷቸው ሰዎች ሁሉ በማጋራት ከጠላፊዎች ይታደጓቸው።

3
2June 16, 2026 3.9K 12