ፈገግ በይ ሁሌ ፈገግታሽ አይጨልም
የበረደው ነፍሴን..
ያሞቀው ጥርስሽ ነው ፀሀይ እኮ አይደለም
አንቺ የሰው ልኬት የእንስቶች አውራ
ስለደግነትሽ እንዴት ብዬ ላውራ?
ምንስ ቃል ቢሰደር የትኛውም ስንኝ
አይገልፅሽምና በጥሞና ስሚኝ
ልመርቅሽ ነውና ባላረጀ እድሜዬ
አሜን ብቻ በዪ 'ባይሆን እንደ እምዬ
የነካሽው ሁሉ እንደ ውበትሽ ይመር
በእድሜሽ ላይ እድሜሽ እንደ ኤሊ ይጨምር
በየደረሽበት ዓለም ሁሉ ያርግድ
አንቺ ያለሽበት ሀዘን ሁሉ ይታገድ
ሊጥልሽ የመጣ ተንገዳግዶ ይውደቅ
ፊትሽ በፈገግታ ዘለአለሙን ይድመቅ
አሜን በዪ ኑሪልኝ የኔ ወርቅ።😘
የጓደኝነት ጥግ❤️
✍️Giyanna
19/12/2018
@Myppoem @Myppoem
@FreamaHasaboch







