ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ እና የፔሉም ኢትዮጵያ ኮንሶርሲየም በማህበረሰብ መሠረት የበግ ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራምና የአገር በቀል ዕውቀት ልማት ላይ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ እና የፔሉም ኢትዮጵያ ኮንሶርሲየም በማህበረሰብ መሠረት የበግ ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም (Community-Based Sheep Breeding Program – CBBP) እና የአገር በቀል ዕውቀትን በማልማት፣ በመመዝገብ እና በማስፋፋት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ (MoU) ተፈራርመዋል።
የመግባቢያ ሰነዱ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. (6 August 2026) በአዲስ አበባ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር ዋቆ ገዳ እና በፔሉም ኢትዮጵያ ኮንሶርሲየም ዳይሬክተር ዶ/ር ኃይሉ አራያ ተፈርሟል።
ይህ ትብብር የጋራ ምርምርን፣ የማህበረሰብ ተሳትፎን እና ዘላቂ የእንስሳት ልማትን ለማጠናከር እንዲሁም የአገር በቀል ዕውቀትን ለመጠበቅ፣ ለማሳደግ እና ለተግባር ለማዋል ያለመ ነው። በዚህ ትብብር ሁለቱ ተቋማት የበግ ዘረመል ማሻሻያን በማጠናከር፣ የገጠር ማህበረሰቦችን ኑሮ በማሻሻል እና ዘላቂ የግብርና ልማትን በመደገፍ በጋራ ይሰራሉ።
የስምምነቱ አካል በመሆን፣ የCommunity-Based Sheep Breeding Program (CBBP) አርሶ አደሮች ቡድን ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ከICARDA ጋር በመተባበር ያቋቋመውን የማጂ የበግ ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም (Maji Sheep CBBP) ይጎበኛሉ።
ይህ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት ተሳታፊዎች ልምዶቻቸውን እንዲለዋወጡ፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን እንዲጋሩ እና በማህበረሰብ መሠረት የበግ ዝርያ ማሻሻያና አስተዳደር ዙሪያ ያላቸውን ዕውቀትና ክህሎት እንዲያጠናክሩ ያግዛል።
Mizan Tepi University and PELUM Ethiopia Consortium Sign MoU to Strengthen Community-Based Sheep Breeding and Indigenous Knowledge Development
Mizan Tepi University and the PELUM Ethiopia Consortium have signed a Memorandum of Understanding (MoU) to collaborate on the implementation of a Community-Based Sheep Breeding Program (CBBP) and the development, documentation, and promotion of indigenous knowledge.
The MoU was signed on 6 August 2026 in Addis Ababa by H.E. Dr. Wako Geda, President of Mizan Tepi University, and Dr. Hailu Araya, Director of the PELUM Ethiopia Consortium.
The partnership aims to strengthen collaborative research, community engagement, and sustainable livestock development while preserving and promoting indigenous knowledge.
Through this collaboration, the two institutions will work together to enhance sheep genetic improvement, improve rural livelihoods, and support sustainable agricultural development.
As part of the agreement, a team of Community-Based Sheep Breeding Program (CBBP) farmers will