የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት ተጠቃሚ ታክስ ከፋይ የሚከተሉት ኃላፊነቶች ይኖሩበታል፤
✅የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ እንዲጠቀም የተፈቀደለት ታክስ ከፋይ ለሚያደርገው ማንኛውም ሽያጭ የተመዘገበ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መስጠት አለበት፡፡
✅ የታክስ ባለስልጣኑ በማንኛውም ሰዓት በታክስ ከፋዩ የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት ላይ ፍተሻ በሚያከናውንበት ጊዜ ተገቢውን መረጃ የመስጠት፣ የባለስልጣኑ ሠራተኞች ሥርዓቱን እንዲያዩ/እንዲፈትሹ ፈቃድ የመስጠት እና ለሂደቱ ትብብር የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
✅ በግብይት ወቅት ገዥው በደረሰኝ ላይ ማንነቱን የሚገልጽ መረጃ፣ የመታወቂያ ቁጥር ወይም የስልክ ቁጥር እንዲመዘገብለት ከጠየቀ መመዝገብ ግዴታ አለበት፡፡
✅ የተፈቀደው የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት ከታክስ ባለስልጣኑ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ምዝገባ ሥርዓት ጋር መገናኘት በማይችልበት ጊዜ የተደረጉ ግብይቶችን በሙሉ ከኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ምዝገባ ሥርዓት ጋር እንደተገናኘ በ72 ሰዓት ውስጥ መመዝገቡን እና ለገዥው ኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መስጠቱን ማረጋገጥ አለበት፡፡
📌 ጥብቅ ማሳሰቢያ፦ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት እንዲጠቀም የተፈቀደለት ታክስ ከፋይ በባለስልጣኑ ያልተፈቀደ ማንኛውንም አይነት የሶፍትዌር ለውጥ እና ማሻሻያ ማድረግ አይችልም፡፡

8August 18, 2026 7.4K 27