ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሐምሌ ወር የገቢ ዕቅድ አፈፃፀሙን ገመገመ
********************************
(ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
የሐምሌ ወር የገቢ ዕቅድ አፈጻጸም ከማኔጅመንት አባላት ጋር በጋራ ተገምግሟል።
የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱ በዕቅድና በጀት አፈፃፀም ቡድን አስተባባሪ ኮ/ር ሞላ ተሾመ በዝርዝር የቀረበ ሲሆን በሃምሌ ወር ብር 2,506,893,981.18 ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 2,727,765,743.12 በመሰብሰብ የዕቅዱን 108.81% ማሳካት መቻሉ ተገልጿል፡፡
በሪፖርቱ የሁሉም ስራ ክፍሎች የስራ አፈፃፀም፣ የተመዘገቡ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች በስፋት ተዳሰዋል። የአፈፃፀም ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ ተሳታፊዎች ሀሳብ እና አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ከተነሱ ዋና ዋና ሀሳቦች መካከልም የሰው ኃይል ሙሌት፣ የሥራ ሰዓት በአግባቡ መጠቀም እና የግብር ከፋዮች መረጃ ጥራት የሚሉት ጥቂቶቹ ናቸው። ጠንካራ ጎኖችን በመለየት ክፍተቶችን በመሙላት በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በቅንጅት መሥራትና የመረጃ ክፍተቶችን በተገቢው መንገድ ማጥራት እንደሚገባ ተጠቁሟል። በተለይም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን በተሳካ ሁኔታ ለመፈፀም ሁሉም የሥራ ክፍሎች በቅርበት በመነጋገር ስራዎችን ማከናወን እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል።
በማጠቃለያም የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቶሉ ፊጤ አመራሩ እና ባለሙያው በተዋረድ በቅንጅት፣ በትጋትና ሥነ-ምግባርን በመላበስ ስራውን ማከናወን እንዳለበት አሳስበዋል። ለግብር ከፋዮች ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት መስጠት ልዩ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችንም በንቃት መፈፀም እንደሚገባ ጠቁመዋል ።አክለውም እንደ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ብሎም እንደ ሀገር ከትሪሊየን ባሻገር የተቀመጠልንን የገቢ ዕቅድ ለማሳካት በቀጣይ ወራት የተሻለ ስራ ለመስራት የጋራ ጥረት እና ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ግብር÷ ለሃገር ክብር!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ቲክቶክ፡-https://www.tiktok.com/@mto2education
ኢሜል፡- [email protected]
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2
Telegram
Ministry of Revenues -Medium Taxpayers Branch No2
This is official Telegram Channel of Ministry of Revenues Medium Taxpayers Branch No 2.
Join the channel.

5
1August 18, 2026 6K 3