ለታክስ ከፋይነት መመዝገብ ያለባቸው እነማን ናቸው?
ማንኛውም ሰው ማንኛውንም የንግድ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ቀደም ብሎ በታክስ ከፋይነት መመዝገብ ይኖርበታል። ለዚህም አስቀድሞ የተመዘገበ ካልሆነ በስተቀር በታክስ ሕግ መሠረት ታክስ የመክፈል ኃላፊነት ያለበት ሰው በባለሥልጣኑ ዘንድ ለመመዝገብ ማመልከት አለበት፡፡
• ለታክስ ከፋይነት መመዝገብ ያለባቸው …
👉 በንግድ ወይም በሙያ ሥራ (መቀጠርን ሳይጨምር) የተሰማራ ግለሰብ፣
👉 ቤት በማከራየት ገቢ የሚያገኝ ግለሰብ፣
👉 ተቀጣሪ፣
👉 የመንግሥት የልማት ድርጅት፣
👉 የመንግሥት ባለበጀት መሥሪያ ቤት፣
👉 መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣
👉 የሃይማኖት ተቋማት፣
👉 የንግድ ማህበር፣
👉 በኢትዮጵያ ነዋሪ ባልሆነ ኩባንያ በቋሚነት የሚሠራ ድርጅት፣
👉 የወጪ መጋራት ተጠቃሚዎች፣
👉 በጋራ ሃብትነት ያልተመዘገበ ሃብት ያላቸው ሰዎች፣
👉 ባለ ልዩ መብት፣
👉 በመንግሥታት መካከል የሚደረግ ስምምነት በጽሕፈት ቤት ማቋቋሚያ ስምምነት የሚቋቋም ድርጅት እንዲሁም
👉 የኩባንያ አክሲዮን ባለድርሻ ናቸው።

August 27, 2026 7K 13