የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ፈተና ያስፈተኗቸው ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ (100%) የማለፊያ ነጥብ አስመዝግበዋል።
ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ረድኤት ሳሙኤል 574.4 እንዲሁም ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ትምህርት ቤት ተማሪ ናትናኤል ሙላት 570.16 በማምጣት የየትምህርት ቤታቸውን ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።