Mobile Problem Solution: post #841 — TG.ME

የኮምፒውተራችንን Hard Drive እንዴት በቀላሉ ፓርቲሽን(partition) መክፈል እንችላለን?
📍በመጀመሪያ ፓርቲሽን በመክፈላችን
ምናገኛቸው ጥቅሞች ምንድናቸው ብለን
ስናስብ እንደየ ፍላጎታችን ሚለያይ ሲሆን
ለሁላችንም ሚሰጠን ዋናው ጥቅም ቢኖር
ፉይላችንን ከ ሲስተም ፋይል ያሉ ፋይሉችንን
ለይተን በማስቀመጥ በተላያዩ ምክንያት ቡት
ማረግ ወይም ኦፕሬቲንግ ሲስተማችንን
መነሳት ሲያቅተው ልናጣ ምንችለውን ፉይል
ለመከላከል የምንጠቀምበት መንገድ ነው
📍ለምሳሌ ከፋብሪካው እንደመጣው በ C:
partiton ብቻ እየተጠቀምን ቢሆንና በ
ቫይረስ ምክንያት ሲስተም ፋይል ቢጠፋ
ሌሎች ፐርሰናል ፉይሎችን አጣን ማለት
ነው።
📍ስለዚህ በቀላሉ እዛው ፓርቲሽን
በመፍጠር የግል ፉይል ለብቻ C: ፓርቲሽን
ለብቻ አድርገን በመጠቀም ፋይላችንን
መከላከል እንችላለን ይህን ካልን ስለ
ፓርቲሽን እንዴት ዊንዶውስ ባዘጋጀልን disk
managment በ መጠቀም እንዴት
መስራት እንችላለን ሚለውን ላሳያችሁ
ወደድኩ
📍በመጀመሪያ ባክአፕ መውሰድ አስፈላጊ ነው
ምንም እንኳ ፕሮሰሱ ፋይል ባያጠፋብንም
ለጥንቃቄ ሲባል ወስደን መጀመር አለብን
📍በመቀጠል ወደ my computer iconላይ
ራይት ክሊክ አርገን manage ሚለውን
ክለክ ስናደርግ አዲስ ዊንዶው ይከፈትልናል
ማለት ነው።
📍በግራ ባለው ዝርዝር ውስጥ
disk managment ሚል በመፈለግ ያንን
እንከፍታለን በመቀጠልም በሚከፈተው
ዊንዶው ውስጥ መሀል ላይ ሁኖ ከታች ባለው
ቦታ ላይ
📍 ያልተከፈለው ፓርቲሽን በ ሰማያዊ
ይታየናል ስለዚህም ማድረግ የፈለግነውን
ፓርቲሽን ላይ ራይት ክሊክ በማድረግ
በሚመጡት ዝርዝሮች ውስጥ shrink
volume የሚል ን በመምረጥ በሚከፈትልን
ዊንዶው መሰረት እንደምን ፈልገው ሳይዝ
በማስገባት ሌላ አዲስ ፓርቲሽን እንፈጥራለን።
⚠️ ማሳሰቢያ የ disk size ስባስገባ ቁጥሩ በ Mega byte(MB) ነው የሚቀመጠው ስለዚህ ለምሳሌ 100 GB ማድረግ ከፈለግኩኝ 1024,000 ብየ ቁጥሩን ማስገባት አለብኝ ማለት ነው ወይም 200GB ማድረግ ብፈልግ 2048,000 ማለት አለብኝ። የ 1 GB ማለት 1024 MB ስለሆነ።⚠️
ይህንን finish ብለን ከጨረስን በኋላ
የከፈትነው ፐርቲሽን እዛው disk
managment ውስጥ በጥቁር ከለር
ይታየናል ስለዚህ ይህንን ፓርቲሽን ላይ ራይት
ክሊክ በማድረግ የጀመረነውን ፓርቲሽን
መፍጠር ለመጨረስ እንጀምራለን።
📍ስለዚህ ራይት ክሊክ ስናደርግ new volume
የሚለውን ስንነካ አዲስ ዊንዶ ይመጣል
ስለዚህ ምንም ነገር ሳንነካ nextን ብቻ
በመጫን መጨረሻም ላይ finish ን
ስንጫን አዲሱ ፓርቲሽን my computer
ውስጥ መታየት ይጀምራል ማለት ነው ።
ጥያቄና አስተያየት ካላችሁ እንደተለመደው
በመጠየቅ አበረታቱን ስል እላለው
አመሰግናለው።
https://t.me/mobileproblemsolution
👍10❤3
August 9, 2023 2.9K 11