አንችም “ሚስት”በደንብ ተዘጋጂ ⁉️ ➦አንተም እውነተኛ «ባል» ሁን በአሏህ⁉️… — Mirjan Digital — TG.ME

➥አንችም “ሚስት”በደንብ ተዘጋጂ ⁉️ ➦አንተም እውነተኛ «ባል» ሁን በአሏህ⁉️ ------------------------------- ⭕️«ብታሰራጩት ብዙዎች ይማሩበታል»⭕️ ወዳጄ…ትዳር ማለት “የነፍስ ውህደት” እንጂ “የአካል ግብዣ” አይደለም። ብዙ ወንዶች “ቆንጆ” ፈልገው ያገባሉ፤ እኔ ግን የምፈልገው “የህይወት አጋር” ነው በላቸው። የቤቴ ንግስት፣ የልጆቼ መምህር እና የህሊናዬ እረፍት ለምትሆን ሴት፣ የማይናወጡ (መስፈርቶች) እነዚህ ናቸው ነው ማለት ያለብህ። ...✍️ጀግና ልብ ያላት ብቻ ታንብበው‼️ ❶. ያልተነካች (Virginity): ይሄ የክብር ጉዳይ ነው። “ዘመናዊነት” በሚል ሰበብ ማንንም ያስስተናገደች ሴት፣ የቤቴ እመቤት አትሆንም። ታማኝነት የሚጀምረው እኔን ከማወቅሽ በፊት ለራስሽ ከነበረሽ ክብር ነው የሚል አቋም ያዝ። ❷. አእምሮአዊ ልዕልና (Intellectual Depth) • የንባብ ሱሰኛ: ከ “ቲክቶክ” እና “ወሬ” ይልቅ፣ መጽሐፍ እና እውቀት የሚረባት። ከእኔ ጋር ስለ ቁርዓን ስለ ሀዲስ፣ ስለ ሰለፎች አቋም፣ስለ ኢስላማዊ ታሪኮች፣ስለ ሳይንስ፣ ስለ አለም እና ስለ ህይወት ትርጉም መወያየት የምትችል እንቁ ሴት። ➨የዝምታ ጥበብ፦ መቼ መናገር እና መቼ ዝም ማለት እንዳለበት የምታውቅ። የሴት ልጅ ግርማ ሞገሷ ጥበብ የተሞላበት ዝምታዋ ነው ይህችን ሴት አስስ ፈልግ እሷን አስብ። ➌. ተፈጥሮአዊ ውበት ያላት (Authentic Beauty) 🌿🚫💅 ►ከፕላስቲክ የጸዳች፣ ► ሜካፕ፣ ►አርቴፊሻል ጸጉር፣ ►የውሸት ጥፍር… እነዚህ የራስ መተማመን ማነስ ምልክቶችና የሴትነት ውርደቶች ናቸው። እኔ የምፈልገው ፈጣሪ የሰራትን “ኦሪጅናል” እንጂ፣ በቻይና ፋብሪካ የተለበጠችውን አይደለም የሚል ፅኑ አቋም ያዝና ፅናበት። ⭕️የማይጠገብ ውበት፣ ስትታይ አይን የምትሞላ፣ ግን ውበቷ ለባሏ ብቻ የሆነ ተሸፋፋኝ ቆንጆ ኒቃቢስት። ❹➨ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቋም (Status & Stability) 💰🏰 • ከክቡር ቤተሰብ የወጣች: “ደግነት የሞላት”ተቆንጥጣ ያደገች ቤተሰብ ይቆጣኛል ብላ የምትሰጋ ቁሳቁስ መቁጠር የሞኝ መርህ ነው። መልካም ዛፍ መልካም ፍሬ ያፈራል እንድባል ከመልካም ቤተሰብ የበቀለች። ከወሮበላ ፣ከክፉ እና ከእምነት አልባ ቤተሰብ ጋር ተጋብተህ፣ ህይወቴን በስቃይ የተሞላና የማገገሚያ ማዕከል ከማድረግ ተጠንቀቅ‼️ ⭕️►የገንዘብ አያያዝ ብስለት ያላት አወ ገንዘብን እንደ መሳሪያ እንጂ እንደ አምላክ የማታይ ስስታም ሳትሆን ቆጣቢ፣ አባካኝ ሳትሆን ለጋስ የሆነች ምረጥ። ❺►. ስሜታዊ ጥንካሬ (Emotional Resilience) 🛡️❤️ • የማትነካካ (No Drama): በትንሽ ነገር የምትነጫነጭ፣ “እንትን አላደረግክሊኝም” ብላ የምታለቅስ ህፃን አትፈልግ በቁም ነገር እየመከርኩህ ነው። ሴት ልጅ ጠንካራ መሆን አለባት። ⭕️►የይቅርታ ልብ ያላት፦ ስህተት የሰው ተፈጥሮ ነው። ችግር ሲፈጠር ግጭት ሲመጣ የምታቀሳስር እንድትሳሳት የምትገፋፋ ሳይሆን የምትደነግጥ ከዚያም አረጋግታህ ቂም ይዞ ከመተኛት ይልቅ ይቅር ብሎ መተቃቀፍን የምትመርጥ ሴት ላይ አተኩር ። ❻►የቤት እመቤትነት (Domestic Queen) 🏠🍲 • የማዕድ ክብር: “በሰራተኛ አሰርቼ አበላሃለሁ” የሚል ዘመናዊነት እኔ ቤት አይሰራም የሚል አቋም ያዝ። የባል ጉሮሮ የሚከፈተው በሚስት እጅ ነው። ምግብ መስራት ሙያ ብቻ ሳይሆን የፍቅር መግለጫ ነው። ⭕️►ልጆች ወላዴና ወዳድ እናትነትን እንደ ሸክም ሳይሆን እንደ ጸጋ የምትቀበል ቆንጆ ሴት መስፈርት አድርግ። ❼►. የማህበራዊ ሚዲያ ንፅህና (Social Media Discipline) 📱🚫 •►ከቲክቶክ የራቀች: የኔ ሚስት “ቲክቶክ” ላይ ወገቧን እያወዛወዘች ለህዝብ “ላይክ” የምትለምን መሆን የለባትም። የቤቴ ክብር በማህበራዊ ሚዲያ ገበያ ላይ አይሸጥም አበደን። •►ምስጢር ጠባቂ: የቤታችንን ጉዳይ ፌስቡክ ላይ እየለጠፈች “Comment” የምትጠብቅ ሴት አልፈልግም። ህይወታችን Private ነው! ➑. ፍፁም ታዛዥነት እና የዘውድ ክብር (Absolute Submission & Respect) 🦁 • የስልጣን ተዋረድ (Hierarchy): የኢስላም-ህግ እንጂ ዲሞክራሲ የሚባል የምዕራባዊያን ፍልስፍና በኔ ቤት ውስጥ አይሰራም። እኔ የቤቱ ካፒቴን ነኝ፤ መርከቡን የምመራው እኔ ነኝ። እሷ ረዳቴ (First Mate) ናት። በ “እኩልነት” (Equal Rights) ሰበብ መሪነቴን የምትፈታተን፣ “ለምን?” እያለች የምትገዳደር እና ስልጣኔን የምትጋፋ ሴት… እኔ ቤት ቦታ የላትም አበደን። ሁለት ራስ ያለው ቤት፣ ትዳር ሳይሆን ጭራቅ ነው። ⭕️ፀረ-ፌሚኒዝም (No Feminist Vibes): “ወንድ የሚሰራውን ሴትም ትሰራለች” የሚል የምዕራባውያን መርዝ ይዛ የምትመጣ ሴት አትሆንልኝም። ወንድ ጠባቂ ነው፣ ሴት ተንከባካቢ ናት። ተፈጥሮ የሰጠንን ቦታ የማትቀበል ከሆነ፣ መውጫው ክፍት ነው። ➨•#ንጉሳዊ_አክብሮት፦ በሰው ፊት ድምጿን ከፍ አድርጋ የምትናገር፣ ወይም የምታቋርጠኝ ሴት ክብሬን ነካች ሳይሆን እራሷን አዋረደች ማለት ነው። ባል ማለት የቤት ንጉስ ነው። ንጉስን የሚያከብር ደግሞ ንግስት ብቻ ናት። እኔን እንደ ንጉስ ካልያዘችኝ፣ እሷን እንደ ንግስት የምይዝበት ምክንያት የለኝም። ❾►. የራዕይ አጋርነት (Vision Alignment) 🔭🚀 • ህልም ያላት፦ እኔ አለምን የመቀየር ህልም አለኝ። እሷ “ቡና እንጠጣ” ከሚል ተራ ወሬ አልፋ፣ ስለ ቢዝነስ፣ ስለ ኢንቨስትመንት ብሎም ስለ አለም አቀፍ ጉዳዮች የምትረዳኝ መሆን አለባት። ⭕️►አበረታች: ስወድቅ የምታነሳኝ፣ ስደክም ጉልበት የምትሆነኝ። “አንተ ትችላለህ” ብላ የምትገፋፋኝ ሞተር ነች ሚስት ማለት ሰምተሀል። ❿►. የባህል አምባሳደር (Cultural Guardian) 🇪🇹☕ • ወግ አጥባቂ: የኢስላምን ቀኖና ሳትጥስ ዘመናዊነትን ከባህል ጋር ያጣጣመች። እንግዳ ሲመጣ እንዴት መቀበል እንዳለበት፣ ማዕድ እንዴት እንደሚቀርብ የምታውቅ። “ፒዛ” ብቻ ሳይሆን “ዶሮ ወጥ” በደንብ የምትሰራ። •⭕️►ቋንቋ እና እሴት: ለልጆቻችን አማርኛ፣ ታሪክ እና ባህል የምትተክል፣ ልጆቼ የፈረንጂ ቋንቋ እንድማሩ እንጂ “ፈረንጅ” ሆነው እንዲያድጉ የማትፈቅድ። ❶❶. የጓደኝነት ወሰን (Boundaries) 🚧👯‍♀️ • የጓደኛ ብዛት: “የሴት ጓደኛ” አብዝታ፣ የቤቷን ጊዜ ለወሬ የምታውል ሴት አልፈልግም በል። ጓደኛዋ እኔ መሆን አለብኝ። ⭕️►• የወንድ ጓደኛ?: በፍጹም! “Bestie” የሚባል የወንድ ጓደኛ ያላት ሴት፣ እዛው ከእሱ ጋር ትቆይ። እኔ ቤት ወንድ ጓደኛ ባል ብቻ ነው። ⚠️ ማሳሰቢያ ይሄን ስታነቢ “ይሄ ሰውዬ ትዕቢተኛ ነው” ካልሽ… ትክክል ነሽ፣እኔና መሰሎቼ ላንቺ አይነት አንሆንም ‼️ ግን “ይሄማ የኔ መገለጫ ነው” ካልሽ… አንቺ የጠፋችው ጀግና ሴት ነሽ ማለት ነው። ወርቅ በገበያ አይጣልም፤ ውድ ዋጋ ላለው ሰው ብቻ ነው የሚሸጠው ይገባሻል አይደል⁉️ እኔ ባለኝ አቅም ራሴን ተዘጋጅቻለሁ በል … እኔ እነዚህን መስፈርቶች ያወጣሁት ውስጤ ላይ ያለውን ሀይል Power አይቼ ነው። ምንም ብሆን እኔ ራሴ ለቤቴ ንጉስ ነኝ። ለሚስቴ አንበሳ ነኝ። ንጉስን ለንጉስ በሚመጥን አቀባበል መቀበል የሚስትነት መለኪያ ነው። ⭕️►ለሚስትትህ ላክላትና ምን እንደምትልህ አድምጥ እኔ ተናግሬያለሁ!! ⭕️ኑረዲን አል-ዓረብ.✍️ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

August 20, 2026 59 1