Meseroyal Tech: post #2779 — TG.ME

Telegram 13 አመት ሞላው።

ተወዳጁ የSocial media platform Telegram በወንድማማቾቹ Pavel Durovና Nikoli Durov ከተመሰረተ ዛሬ 13ኛ ዓመቱን ይዟል።

በ2013 ዋና መስርያ ቤቱን ጀርመን በርሊን በማድረግ ስራውን የጀመረው ቴሌግራም ለተወሰኑ አመታት ምንም አይነት ገቢ የማያስገባና በየወሩ ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለስራ ማስኬጅ የሚያስወጣ Social media platform ነበር።

ከሌሎች የማህበራዊ ሚድያ መተግበሪያዎች በተሻለ የተጠቃሚዎቹን መረጃ ሚስጥራዊነት  እንደሚጠብቅ የሚነገርለት ይህ አፕ በአጭር ጊዜ ውስጥ በብዙዎች ዘንድ በመወደድ ስኬት ማስመዝገብ ጀመረ። ከመንግስታዊ ተፅዕኖም ነፃ በመሆኑና ከዋና ተገዳዳሪው Whatsapp የተሻለ ብዙ ፊቸሮች ስለጨመረ በብዙዎች ዘንድ ለመወደድ በቃ። 

በሚቀጥሉት ጥቂት አመታትም በተጠቃሚ ቁጥር በሜታ ስር ከሚተዳደሩት facebook messenger እና WhatsApp ሊበልጥ እንደሚችል ይጠበቃል።
በአሁኑ ሰአት ዋና መስሪያ ቤቱን በዩናይትድ አረብ ኢሚሬት ዱባይ ከተማ በማድረግ ከተራ የመልዕክት መለዋወጫ አፕሊኬሽንነት ከፍ በማለት የክሪፕቶከረንሲ ቢዝነስ አካቶ እየሰራ ይገኛል።

በአሁኑ ሰአት እጅግ ትርፋማ ከሆኑት የsocial media ፕላትፎርሞች ውስጥ የሚካተተው ቴሌግራም በአለም ዙሪያ ብዙ ሰራተኞች የሚያስተዳደር ትልቅ ድርጅት ሊሆን ችሏል።
የብዙ ሰዎች ህይወትም በዚህ app አማካኝነት እየተቀየረ ይገኛል።

የዋና መስራቹ Pavel Durov አጠቃላይ ሀብት $15.5B እንደሚገመት Forbes ዘግቧል።

Happy Birthday Telegram

እስኪ ቴሌግራም ስትጠቀሙ ስንት አመት ሞላችሁ? አካውንት የከፈተችሁበትን አጋጣሚ ካስታወሳችሁት በcomment አካፍሉን።
🔥2👍1