Telegram ከApp Store ላይ ለጥቂት ጊዜ ከወረደ በኋላ ተመለሰ! Telegram በApple App… — Meseroyal Tech — TG.ME

Telegram ከApp Store ላይ ለጥቂት ጊዜ ከወረደ በኋላ ተመለሰ!

Telegram በApple App Store ላይ ለጥቂት ሰዓታት ታግዶ ከቆየ በኋላ ድጋሚ ወደ ቦታው መመለሱን ኩባንያውና አፕል አስታወቁ።

እንደ Reutersና Bloomberg ዘገባዎች ከሆነ Apple መተግበሪያውን ከApp store ላይ ለጊዜው ያነሳበት ዋና ምክንያት የContent Moderation እና Guidelines ጥሰት እንደሆነ ተጠቅሷል።
Apple ባደረገው Review በTelegram ላይ ከህጻናት ጥቃት ጋር የተያያዙ ተገቢ ያልሆኑ ይዘቶች (Child Sexual Abuse Material) መለቀቃቸውን ተከትሎ የአፕልን ጥብቅ ደንቦች መጣሱን አረጋግጧል።
Apple ችግሩን ካሳወቀ በኋላ የTelegram ደቨሎፐሮች ወዲያውኑ ህገ-ወጥ ይዘቱን ከፕላትፎርሙ ላይ በማስወገድና ይዘቱን የለቀቀውን User Account በዘላቂነት Ban በማድረጋቸው መተግበሪያው በድጋሚ በApp Store ላይ ተመልሷል።

መተግበሪያው በወረደበት ሰዓት ተጠቃሚዎች በApp Store ላይ ቴሌግራምን ሲፈልጉ "The page you're looking for can't be found" የሚል መልእክት ያሳያቸው ነበር።

አጋጣሚው በApple App Store ላይ ብቻ የተከሰተ ሲሆን በGoogle Play Store እና በMac App Store ላይ ምንም አይነት መስተጓጎል አልነበረም።

አካውንታችሁ ban እንዳይደረግ ቴሌግራም ላይ share የምታደርጉትን ነገር ጥንቃቄ አድርጉ።

Share
@meseroyal_tech
@meseroyal_tech
😁5🔥1😢1
August 4, 2026 36