ኬንያ ከTether ጋር በመተባበር USDTን ለSettlement የመጠቀም ሙከራ ጀመረች።
የኬንያው ግዙፍ የአክሲዮንና የሴኩሪቲስ ገበያ Nairobi Securities Exchange (NSE) በአለም አቀፍ ደረጃ በUSDT Stablecoin የሚታወቀው Tether ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነት መፍጠሩን ይፋ አደረገ። ይህ ትብብር 26.4 ቢሊዮን ዶላር ካፒታል ባለው የኬንያ የካፒታል ገበያ ውስጥ ክፍያዎችን (Settlement) በUSDT ለመፈጸም የሚያስችል ታሪካዊ ስምምነት ነው።
ከዚህ ቀደም የኬኒያ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ኢንቨስተሮች በNSE ገበያ ውስጥ Stock፣ Bondና ሌሎች Financial Assets ሲገዙ በFiat Currency ወይም በኬንያ ሽልንግና በአሜሪካን ዶላር ብቻ በኩል የነበረው የSettlement ሂደት ቀናት ይወስድ ነበር። Tether USDTን በመጠቀም ግን አጠቃላይ ሂደቱን በBlockchain ቴክኖሎጂ አማካኝነት በሰከንዶች ውስጥ በዝቅተኛ የTransaction Fee ለማከናወን ያስችላል።
ይህ ስምምነት የዶላር እጥረት በሚያጋጥምበት በአፍሪካ ገበያ ውስጥ USDTን እንደ Settlement Currency መጠቀም የውጭ ኢንቨስተሮች በቀላሉ ወደ ኬንያ ገበያ ገብተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ በር ይከፍታል ተብሏል።
ይህ ሙከራ የሚካሄደው በኬንያ Capital Markets Authority (CMA) የቁጥጥር ማዕቀፍ ስር ሲሆን የደህንነት እና ህጋዊነት መስፈርቶችን የጠበቀ መሆኑ ይረጋገጣል።
NSE ባወጣው መግለጫ "ይህ አጋርነት የኬንያን የካፒታል ገበያ ወደ አዲሱ Digital Economy እና Web3 ማስገቢያ ትልቅ እርምጃ ነው። የTrading እና Settlement ሂደቶችን በማዘመን አጠቃላይ የገበያችንን Liquidity ያሳድጋል።" ብሏል።
Tether በበኩሉ"አፍሪካ ለCrypto እና Stablecoin አጠቃቀም በጣም ፈጣን እድገት የምታሳይ አህጉር ናት። ከNSE ጋር መስራታችን USDTን Trading ብቻ ሳይሆን ለሀገር አቀፍ የካፒታል ገበያ infrastructure ደረጃ ለመጠቀም መንገድ ይከፍታል።" ማለቱን CoinMarket ዘግቧል።
ጎረቤታችን ኬንያ የDigital finance ህጎና ስርዐቶችን በማውጣት ከቴክኖሎጂው እየተጠቀመች ሲሆን እኛ ሃገር ግን ዜጎች ጭራሽ በቴክኖሎጂው ተጠቅመው ሃብት እንዳያፈሩ የተለያዩ ክልከላዎች እየወጡ ነው።
✍እስኪ በዚ ጉዳይ ያላችሁን ሃሳብ በcomment አስቀምጡ።
Share
@meseroyal_tech
@meseroyal_tech
4July 31, 2026 79 1