መውሊድ በበፊት አክባሪዎቹ ሲጋለጥ ከዚህ በታች የምታነቡት መውሊድ የሚሄድ የነበረ ሰው ይፈፅም የነበረውን ሺርክ፣ አላህን ማመፅ፣ የሙስሊሞች ብር ዘረፋ እንዲህ ሲል ያስቀምጠየዋል እኔ ገጠር ያደኩ ሥሆን በዛን ጊዜ ሥለድን ከቤተሠቦቼ እንኳን አንዳችንም አናቅ፡፡ ታዲያ መወልድ ደረሠና ሥንቃችንን ይዘን በጧት ተነሥተን ወደ ጀማ ንጉሥ መጎዝ ጀመረን፡፡ ይሄንን ቁልቁለት ሸቅበት በሥንት ጉድ ጨርሠን፡፡ ማታ ጀማ ንጉሥ ገባን፡፡ ከዛ ማታ ህዝቡ እደ ጉድ ተሠብሥቧል፡፡ ከዛ መንዙማ ተከፈተ ሤቱም ወንዱም እደ ዲልቂያ ተደበላልቆ እሥክታ ይመታ ጀመረ፡፡ ብቻ እኔ ሥለድኔም ምንም ባላቅ አልጣመኝምና ወደ ዳሡ ሄጂ ተኛሁኝ፡፡ ጧት ቀሠቀሡኝ እና እንሄድ አሉኝ፡፡ የት አልካቸው? ወረፉ እንያዝ አሉኝ፡፡ ለምኑ? ሸሆቹ እየመረቁ ነው እኮ አሉኝ፡፡ ሠልፉን ያዘን ከዛ እበራፉ ላይ ሁለት ጥምጣም የጠመጠሙ እየመረቁ የሄንን ብር ለጉድ ሠብሥበውታል፡፡ ከዛም አልፉ ወደ ቤቱ እየተገባ በመሥኮቱ ወደ ውሥጥ ብር ይወረወራል፡፡ እውሥጥ በድቦራ የተሸፈነ ትልቅ ጎራ የሚመሥል አለ፡፡ በዛ በመሥኮት ባለሀጃው መቶ ሥቅሥቅ ብሉ ያለቅሣል፣ ይለምናል፡፡ የሄንን ካደረጋችሁልኝ ኮርማ አቀርባለው፡፡ ብቻ አምልኮ በሙሉ ለፍጡር ይደረጋል፡፡ እኔ በአይኔ ያየሁት ጉዳይ ነው፡፡ ከዛ ለአንድ ጎደኛየ ይሄንን ነገር ነገርኩትና ያማ በድቦራ የተሸፈነው ቀብር ነው አለኝ፡፡ ጀማ ንጎሥ የሽርክ መነሀሪያ መሆኑን አወኩ፡፡ አሏህ ሽቶልኝ ወደ ሣወዲ አምጥቶ ዲኔን አሣወቀኝ፡፡ ጀህልና ወልቅ ብላ ሄደች አልሀምዱሊላህ እና ይሄንን ለመናገር የፈለኩት አንዳንድ ሠዎች መውሊድ እምናከብረው እና ሥናከብር ድሆችን ለማብላት ቁራአን ለመቅራት ወዘተ ይላሉ ወሸት ነው፡፡ የዚህ ወንድም ምስክርነት በዚህ አበቃ፡፡ ከዚህ የምንወስደው ትምህርት ሀገራችን ላይ - ሱፊዬች የተውሒድ ሰዎች ናቸው እያሉ የሚያጭበረብሩት ውሸት ነው፡፡ ሱፍዬች ይሀው ሺርክ እና ቢድኣን አስፋፊ ናቸው፣ - መውሊድ ላይ ቀብር አምልኮ ይፈፀማል፣ - የድሆች ብር ይበዘበዛል፣ - ለሆዳቸው የደሩ አሊም ተብየዎች ይህንን ጥፋት በማስፋፋት ላይ የመጀመሪያውን ድርሻ ይይዛሉ፣ - መውሊድ ላይ ነብዩን እናወድስበታለን እያሉ የሚያጭበረብሩት ኪስ አውላቂዎች የነሱን ሀብት ለማዳለብ እንጂ ለነብዩ ውዴታ አይደለም፣ - መውሊድ በሃበሻ ዲን ለመስፋፋት አስተዋፅኦ አድርጓል የሚሉን ሰዎች ውሸታሞች ናቸው፡፡ መውሊድ ይሀው ዲንን አፍራሽ ለመሆኑ ሰሜን አካባቢ የሚሰራውን የአይን እማኞች የተናገሩት ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው፡፡ አላህ ኡማውን ከማጭበርበር እና በአጭበርባሪዎች ከመጭበርበር ይጠብቀን፡፡ https://t.me/SadatTextPosts
መውሊድ በበፊት አክባሪዎቹ ሲጋለጥ ከዚህ በታች የምታነቡት መውሊድ የሚሄድ የነበረ ሰው ይፈፅም የነበረውን… — Menzuma — TG.ME
Forwarded fromSadatKemal Abu Meryem
September 25, 2022 28.5K 9