#Meta_ኩባንያ የፌስቡክ (Facebook) እና ኢንስታግራም (Instagram) እህት ኩባንያ የሆነው ሜታ (Meta) ከህፃናት እና ወጣቶች ደህንነት ጋር በተያያዘ የተመሰረተበትን ክስ ለመፍታት ግዙፍ የስምምነት ማዕቀፍ (Settlement Framework) ተቀብሏል።የዚህ ስምምነት ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦ ቢሊዮን ዶላሮች የሚደርስ የካሳ ክፍያ ኩባንያው በክሱ ምክንያት እስከ 18 ቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ሊከፍል የሚችልበት ስምምነት ላይ ደርሷል።አዳዲስ ጥብቅ ገደቦች፦ ወጣቶች እና ህጻናት ማህበራዊ ሚዲያዎችን ሲጠቀሙ ከጥቃት፣ ከሱስ እና ካልተገቡ ይዘቶች ለመጠበቅ ሜታ በመድረኮቹ ላይ እጅግ ጥብቅ የሆኑ የደህንነት ገደቦችን ለማስተካከል ተሰማምቷል። የክሱ መነሻ ምክንያት ሜታ ታዳጊዎች በማህበራዊ ሚዲያ ሱስ እንዲያዙ በማድረግ እና የአእምሮ ጤናቸው ላይ ጉዳት በማድረስ በተለያዩ የዓለም ሀገራት (በተለይም በአሜሪካ ግዛቶች) ክስ ቀርቦበት የነበረ መሆኑ ይታወሳል። ይሄን ውሳኔ እናንተ እንዴት አያችሁት በ comment አጋሩኝ። @Senaytech
August 30, 2026 30