ከመመገብ መፍጠር ይቅደም
አብዛኛዎቹ ሰዎች በቀን ከ 4 እስከ 6 ሰዓታት የሌሎች ሰዎችን ይዘት፣ ህልሞች እና አስተያየቶች በመመገብ ያሳልፋሉ - ከዚያም ለምን ድካም እንደተሰማቸው እና ተነሳሽነት እንደሌላቸው ያስባሉ።
ሌሎች ሲያሳኩ ዘወትር ስትመለከት፣ በንፅፅር ወጥመድ ውስጥ ትወድቃለህ። ነገር ግን የራስህን የሆነ ነገር በመገንባት፣ በመጻፍ ወይም በመንደፍ ለ10 ደቂቃዎች እንኳን ስታሳልፍ፣ ማንነትህን ከተመልካች ወደ ተጫዋች ታዛውራለህ።
መፍታት ስለምትፈልገው ችግር 3 አረፍተ ነገር ማስታወሻ ፃፍ ፣ የሆነ ነገር ሳል ፣ አዳዲስ የይዘት ሀሳቦችን ፃፍ። ፈጠራን ቀዳሚ አድርገውና መመልከት ሁለተኛውን ደረጃ ይውሰድ።
ማህበራዊ ሚዲያ ከመክፈትህ በፊት፣ ወይም ቪዲዮዎችን ከመመልከትህ በፊት፣ ለአፍታ አቁምና የመጀመሪያዎቹን 15 ደቂቃዎች የሆነ ነገር በመፍጠር አሳልፍ። ፈጠራ በራስ መተማመንን ይገነባል። ዓለምን የሚቀርጽ አምራች በመሆን ቀንህን ትጀምራለህ።
ቀንህን የምትጀምረው ሌሎች ሰዎች የሚያደርጉትን ነገር በመመገብ ከሆነ ድብቁ አዕምሮህ አንተ ያለህበትን ደረጃ ከእነርሱ ጋር ያነፃፅራል።
መጀመሪያ የሌሎችን ይዘት ስትመገብ አእምሮህን በሌሎች ሰዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች እና ጫጫታ ትሞላለህ። መጀመሪያ አንተ ስትፈጥር ግን ትኩረትህን እና የአእምሮ ጉልበትህን መልሰህ ታገኛለህ።

6
3August 5, 2026 962 1 1