Mack Computer Technology 🧑‍💻: post #361 — TG.ME

ለውድ ደንበኛችን፡ የጥንቃቄ መልዕክት አለን።
*
‎ከሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ጋር በተያያዘ እርስዎ በአካል ወደ ባንካችን ቅርንጫፎች ሳይመጡ በስልክ ተደውሎ የሚሰጥ ምንም አይነት አገልግሎትም ሆነ የአሠራር ሂደት የሌለን መሆኑን እያሳወቅን፤ የይለፍ ቃልዎን ለሌላ ሶስተኛ ወገን ተጋላጭ ባለማድረግ በጥንቃቄ እንዲገለገሉ እናሳውቃለን፡፡ እንዲሁም “ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው” በሚል በስልክ በሚላክ መጠይቅ ምንም አይነት መረጃዎን እንደማንጠይቅዎ በመረዳት እራስዎን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቁ እናሳስባለን፡፡
‎በተጨማሪም ፦
⦁ ከባንክ ነው በሚል የሚደርስዎትን የስልክ ጥሪ ትክክለኛነት ወደ ባንካችን ቅርንጫፍ በመሄድ ወይም ወደ 951 በመደወል ሳያረጋግጡ ምንም ዓይነት እርምጃ አይውሰዱ፣
⦁ የአፕሊኬሽንም ሆነ USSD ‎ተጠቃሚ ከሆኑ የይለፍ ቃልዎን ከአራት እስከ አስር ዲጂት(ቁጥሮች) ይጠቀሙ፤
⦁ የሞባይል መተግበሪያዎችን (Applications) ወይም ማስፈንጠሪያዎችን (Links) ከማይታወቅና ትክክለኛ ካልሆኑ ምንጮች ስልክዎ ላይ አይጫኑ፤
⦁ ማንኛውንም አይነት መተግበሪያ ከ-Playstore እና ከAppstore ብቻ አውርደው ይጠቀሙ፤
⦁ የዲጂታል የባንክ አገልግሎት የሚስጥር ቁጥርዎን ለማንም አያሳውቁ፤ ሞባይል ስልክዎ ላይ ወይም ማንኛውም ነገር ላይ አይፃፉ፣ ጠንካራ የሚስጥር ቁጥር ይጠቀሙ፣
⦁ ጓደኛ ወይም ዘመድ በመምሰል በማንኛውም አይነት የማህራዊ ሚዲያን በመጠቀም የገንዘብ ዝውውር/ብድር ሲጠየቁ ክፍያውን ከመፈፀምዎ በፊት መልዕክቱ ከትክክለኛ ወገን የተላከልዎት መሆኑን ያረጋግጡ፤
⦁ በተለያዩ ስልቶች ከሚፈፀሙ ስርቆቶችና ማጭበርበሮች እራስዎን ይጠብቁ፤
⦁ የአሻራ ደህንነት ማጠናከሪያን ይጠቀሙ፤
⦁ መረጃ ለማግኘት የባንካችንን ቅርንጫፎች፣ በነጻ የስልክ መስመር ወደ 951 በመደወል እና ትክክለኛ የባንካችንን የማህበራዊ ትስስር ገፆች ይጠቀሙ፡፡
⦁ የአካውንት ገቢና ወጪ ሒሳብዎን ሁሌም ይከታተሉ፤ የቀሪ ሒሳብዎን ትክክለኛነት በማረጋገጥ የማያውቁት ተቀናሽ ካለ፣ ስልኮት ከጠፋ/ከተሰረቀ፣ ከሒሳብዎ ጋር የተገናኘ ሲም ካርዶ ከጠፋ ወዲያውኑ 951 በመደወል ወይም በአቅራቢያዎ ወደ ሚገኘው ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ ያሳውቁ፤
⦁ የ*889# ብቻ ተጠቃሚ ከሆኑ እባክዎ ለደህንነትዎ ይበልጥ አስተማማኝና ቀልጣፋ እንዲሁም ተጨማሪ አገልግሎት ወደሚያስገኝልዎ የሞባይል መተግበሪያ ይዛወሩ፡፡
መተግበሪያውን ለማግኘት፦
ለAndroid፦https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.mobilebanking
ለIOS፦https://apps.apple.com/us/app/cbe-mobile-banking-new/id1534203410
*
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!!
Google Play
Commercial Bank of Ethiopia - Apps on Google Play
With CBE Mobile app you can perform banking tasks anywhere at anytime!
July 30, 2026 74