-- ማሳሰቢያ --
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርዜጎች በሃገር ውስጥ እና በውጭ በሚፈጠር የሥራ ዕድል በህጋዊ መንገድ መብታቸው ደህንነታቸው እና ጥቅማቸው ተጠብቆ መስራት እንዲችሉ የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ስምሪት ስምምነት በመፈፀም ለፓስፖርት እና ለጤና ምርመራ ከሚከፈል ክፍያ ውጪ በነፃ አገልግሎት እንዲያገኙ እያደረገ ይገኛል፡፡
በዚህ አገልግሎት በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት የባዮሜትሪክስ መረጃዎቻቸውን የሰጡ፣ ማንነታቸው የተረጋገጠ፣ ስልጠና የወሰዱ ከ189,430 በላይ ዜጎች ባለፉት 6 ወራት ወደ ተለያየ ሃገር ተሰማርተዋል፡፡ በስምሪቱ ከፍተኛ ስኬት ያስመዘገቡ ክልሎች እንደሚከተለው ይቀርባሉ፡፡
ኦሮሚያ ክልል = 94,106
አማራ ክልል = 39,205
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል = 27,500
ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል = 14,947
አዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር = 6,331
ደቡብ ምዕራብ ክልል = 3,613
ሲዳማ ክልል = 1,430
ትግራይክልል = 822
ሐረር ክልል = 286
አፋር ክልል = 205
ድሬዳዋ ከተማ መስተዳደር = 193
ሱማሊ ክልል = 193
ቤንሻንጉል ክልል = 181
ጋምቤላ ክልል = 83
በዚህ በውጭ ሃገር የሥራ ስምሪት በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ግብዓት በማሟላት ከዚህ በፊት ወደ ውጪ ሃገር ሰራተኛ አሰማርተው የማያውቁ ክልሎች ጭምር የዕድሉ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ምቹ ሁኔታ የፈጠረ በመሆኑ የስምሪቱ ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ዜጎች በአቅራቢያቹ በቀበሌ ደረጃ በሚገኙ አንድ ማዕከላት በመሄድ እንድትመዘገቡ ጥሪ እናቀርባለን::
ከዚህ ውጪ የሚደረግ ወደ የትም ሃገር "ለስራ እናሰማራቸዋለን" እና "በቀላሉ ስራ እንድታገኙ እናማክራቸዋለን” የሚል ቅስቀሳ ዜጎችን ለከፋ አደጋ የሚጥል እንዲሁም ከፍተኛ የገንዘብ ማጭበርበር በመሆኑ ራሳቸውን እንድትጠብቁ እናሳስባለን፡፡
የባዮሜትሪክስ ምዝገባ የሚያከናውኑ አንድ ማዕከላትን ዝርዝር (https://lmis.gov.et/ossc-lists ) ከዚህ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!!
Forwarded from|| ZOLLA TUBE ||
15
1March 6, 2024 2.5K 2 6