በኢትዮጲያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት(E-LMIS) የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ አንድ ማዕከላት
ተግባራዊ እየተደረገ በሚገኘው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (E-LMIS) በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች የባዮሜትሪክስ ምዝገባ ካደረጉት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ተመዝጋቢዎች የመዘገቡ 30 የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች እና ሠራተኞችን እውቅና ስንሰጥ በታላቅ ደስታ ነው !!
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢትዮጲያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱን ለማዘመን ባደረገው ጥረት ወደ ሥራ ከገቡ አንድ ማዕከላት መካከል የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገብ ግንባር ቀደም በመሆናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ።
ይህ የላቀ አፈፃፀም የምትሰጡትን አገልግሎት ፈጣን፣ ቀልጣፋና ፍትሃዊ በማድረግ የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ እና ሥራውንም ለማዘመን ካላችሁ ቁርጠኝነትና ትጋት የሚመነጭ መሆኑ እሙን ነው።
የእናንተ ትጋትና ቁርጠኝነት የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የሰው ሀብት አስተዳደር፣ የክህሎት ልማት እና የሥራ እድል ፈጠራ ላይ የሪፎርም ስራዎችን በማከናውን ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታልና ስለምታደርጉት አስተዋፅዖ ከልብ እናመሰግናለን !
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚
8
4
2February 10, 2024 1.9K 2

