"ሥራ በክህሎት ይመራ!"
"ሥራ በክህሎት ይመራ!" በሚል መሪ ሀሳብ በሠመራ እየተካሄደ የሚገኘው የ2016 በጀት ዓመተ የመጀመሪያ ስድስት ወራት የዕቅድ አፈፃፀም የግምገማ እና የምክክር መድረክ እንደቀጠለ ነው።
በመድረኩ የክህሎት ልማት፤ የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ እንዲሁም የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፎች የየክልሉን የዕቅድ አፈፃፀም እያቀረቡ ይገኛል።
ይህን ተከትሎ በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፉ ላይ የተገኙ መልካም አፈፃፀሞችን ማላቅ፣ ዝቅተኛ አፈፃፀሞችን ማሻሻል እና ምርጥ ተሞክሮዎችን መለየት የሚያስችል ውይይት የሚካሄድ ሲሆን የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ይለያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ጥር 30/2016 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
Youtube https://youtube.com/@mulualemdergu?si=-oRy0LCsTIf-9A13
4February 8, 2024 2.6K