ያዕቆብ በያቦቅ ወንዝ ማዶ ብቻውን በቀረበት ምሽት እግዚአብሔር የያዕቆብን ታሪክ ብቻ ሳይሆን👉 የትውልዱን… — የበጉ ብርሃን እንተርናሽናል || LIGHT OF LAMB MINISTRY — TG.ME

✨ያዕቆብ በያቦቅ ወንዝ ማዶ ብቻውን በቀረበት ምሽት እግዚአብሔር የያዕቆብን ታሪክ ብቻ ሳይሆን👉 የትውልዱን እጣ ፈንታ እየቀየረ ነበር። “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል” (ዘፍጥረት 32፥28) ያዕቆብ ማለት አታላይ ማለት ነበርና ይህን ባለው ጊዜ ያዕቆብ ከአንድ ተራ ኮብላይነት ወደ👉 “ታላቅ የነገድ አባትነት” ተሸጋገረ!!! እስራኤል ተባለ!!! እግዚአብሔር የያዕቆብን ስም የቀየረው እርሱ ብቻውን ተለውጦ እንዲቀመጥ ሳይሆን ከአብራኩ የሚወጡት 12ቱ ልጆቹ 👉“የእስራኤል ነገዶች” ተብለው እንዲጠሩና የመለኮታዊ ቃል ኪዳን ተሸካሚ እንዲሆኑ ነው። " በአንተና በዘርህ የምድር አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ።” ዘፍጥረት 28፥143 ስሙ👉 “እስራኤል” ተብሎ ከተቀየረ በኋላ ያዕቆብ ለራሱ መኖር አቆመ። ልጆቹን ሰብስቦ ስለ ወደፊቱ ጊዜ መተንበይና መባረክ ጀመረ። በዘፍጥረት ምዕራፍ 49 ላይ 👉ያዕቆብ ከመሞቱ በፊት አሥራ ሁለቱን ልጆቹን በየስማቸው እየጠራ የወደፊት እጣ ፈንታቸውን ሲተነብይና ሲባርክ እንመለከታለን። ወዳጆቼ ትናንት የነበራችሁበት ማንነት፣ ውድቀት ወይም ድካም ብቻ ምንም ይሁን ምን ወደ🤌 እግዚአብሔር ፊት በቅንነት ስትቀርቡ እርሱ ድካማችሁን በኋይሉ ያበረታል ስማችሁን ነገራችሁን ሁሉ በመልካም ይቀይራል። ትግላችሁን ወደ በረከት፣ እፍረታችሁን ወደ ክብር ይለውጠዋል። ━ ━ ━━⊱✿⊰━ ━ ━ ━ 🔥🔥#Join_now🔥🔥         ✓  @lightoflamb ✓        ✓   @lightoflamb  ✓

❤6🙏5
August 21, 2026 1.3K 1 10