ጳጉሜ 1 ስለ ሁሉ ነገር እግዚአብሔር ይመስገን🙏
ወደ ኋላ ተመልሰን እየተገባደደ ያለውን ዓመት ስናስብ እግዚአብሔርን ለተከፈቱልንም ለተዘጉብን በሮችም እናመስግነው ለተቀበልነውም ለጠፋብንም ነገር እናመስግነው። ለደስታችን ቅርብ ስለነበር በእንባችን መካከልም ስለተገኘልንም እናመስግነው። ለጸሎታችን መልስ ስለሰጠ አሁንም መልስ ለምንጠብቀበት ልመናም እንዲሁ እናመስግነው። ለሰጠን ሰዎች እናመስግነው። ከእኛ ለወሰዳቸውም ሰዎች እንዲሁ እናመሰግነው።ለምናውቀው በረከት እኛ ከማናውቀው ክፉ ነገር ስለጠበቀንም እናመስግነው። ዛሬ ምክንያት ስላለን ብቻ አይደለም የምናመሰግነው እግዚአብሔር እግዚአብሔር ስለሆነ እናመሰግነዋለን። በምንረዳውም ሆነ በማንረዳው ነገር ሁሉ ውስጥ ሁሉ እንደሚሠራ ስለምናምን እናመሰግነዋለን ይህን ዓመት በራሳችን ጥንካሬ ብቻ አልተሻገርነውም ጸጋው ነው ያበረታን የደገፈን እዚህ ያደረሰን። ስንወድቅ እያነሳን ስንደክም እያበረታን ስንፈራ እያረጋጋን ስንጠፋ መንገድ እያሳየን ስናዝን እያፅናናን ስንደሰትም እንዲሁ ከእኛ ጋር ነበር በመጡትም በሄዱትም ሁኔታዎች ውስጥ ሁሉ ከእኛ ጋር ነበር ስለዚህ ዛሬ እንዲህ እንለዋለን ስለ ሁሉ ነገር እናመሰግንሃለን ስለሰጠኸን፣ ስለከለከልከን፣ስለከፈትክልን፣ ስለዘጋህብን፣ ስለመራኸን፣ ስለጠበቅከን እዚህ ስላደረስከን ስምህ ለዘላለም ይባረክ። ከዚህ በውሀላ የሚመጣውን ነገር ባንረዳም አንተን እናምናለን ነገ ምን ይዞ እንደሚመጣ ባናውቅም ባንተ ብቻ የተሻገርናቸው ቀናቶች እያየን እናምናምሀለን ያለፈውን ሁሉ ለአንተ እንሰጣለን የሚመጣውንም በእጅህ ላይ እንተዋለን። እኔና ይሄን ፅሁፍ የሚያነቡ እህት ወንድሞቼ ስለ ሁሉም ነገር እናመሰግንሃለን። 🤍
“በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።” — 1 ተሰሎንቄ 5፥18
36
8
1