ሰዎችየ ይችን ብቻ ልንገራችሁማ፣ ሰዎች ሌትም ቀንም ብለው ለፍተው ወደ ህልማቸው ሲቃረቡ ፈተናው ከፍ ይላል… — Kidus's Chronicles — TG.ME

Forwarded fromBIBirhan Nega
ሰዎችየ ይችን ብቻ ልንገራችሁማ፣ ሰዎች ሌትም ቀንም ብለው ለፍተው ወደ ህልማቸው ሲቃረቡ ፈተናው ከፍ ይላል አይደል። ሩጫ ላይ ካያችሁ በጣም ከባዱ ፈተና የመጨረሻው 100 ሜትር ላይ ነው። ትንፋሽ እያለቀ፣ ጉልበት መዛል ጀምሮ ፍጥነት ግን ግደታ ሲሆን አስቡት።

በአንድ ወቅት ኢንተርኔት ፍለጋ ቢሮ ሳድር እንደነበር ነግሬያችሁ ነበር፣ አልሃምዱሊላህ ያን ድካሜን አላህ ቆጥሮልኝ እነዛ ቀናት ታሪክ ሆነዋል። አሁን የማየው እኔ ያኔ ያሳለፍኩትን ትግል የሚታገሉትን ነው። ያለፈበት ያውቀዋል።

ይሄን ያነሳሁት፣ ዛሬ ጠዋት ማይክ የጻፈውን ብሎግ ሳነብ ትዝ ብሎኝ። ማይክ የ19 አመት ልጅ ነው። የራሱን ስታርታፕ ከኮፋውንደሩ ጋር በብዙ እልህ አስጨራሽ ትግል ዳር ደርሶላቸው በአንትለር 1.5 ሚሊዮን ዶላር Valuation ማግኘት ችሏል። አሁን ችግሩ እዛ ሄዶ ለመኖር የሚፈልገው ነገር ቀላል አልሆነለትም። እሱ ማንንም የመጠየቅ ሀሳብ አልነበረውም። ላይፍ አንዳንደ እንድህ ነው ። ነገ በሚሊዮኖች ልታገኙ ነገር ዛሬ 50 ብር ልትቸገሩ ትችላላችሁ።

እንደ አንድ የታናናሾቹ ጉዳይ የሚያሳስበው ባለሙያ ያወራኝን ላጋራችሁና መደገፍ የሚችል በሀሳብም በገንዘብም ልንደግፈው የሚገባ ልጅ ነው ብየ አስባለሁ። የበኩሌን በሁለቱም ለማገዝ ሞክሬያለሁ።

ቀሪውን ግን Over to you ቤተሰብ
1❤7
September 30, 2026 131 1