በክርስቶስ IN CHRIST ከፍል 96 ትንቢት፣ልሳን መናገር እና ልሳን መተርጎም 1) ትንቢት መናገር 1ቆሮ… — #KALTUBE — TG.ME

በክርስቶስ   IN CHRIST
ከፍል 96

ትንቢት፣ልሳን መናገር እና ልሳን መተርጎም

1) ትንቢት መናገር 1ቆሮ 12:10
2) በልዩ ልዩ አይነት ልሳን መናገር 1ቆሮ 12:10
3) በልሳን የተነገረውን መተርጎም 1ቆሮ12:10


1-ትንቢት  የመናገር ስጦታ 1ቆሮ 12:10

ትንቢት መናገር ማለት ከተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚሄድ የእግዚአብ ሔርን ሉአላዊ ሃሳብ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ማወጅ/ መናገር ነው። ትንቢት መናገር እግዚአብሔር እንድናደርገው በቃሉ ያዘዘውን ነገሮች ለሰዎች ማወጅ/ መናገር ነው።

➛ ትንቢት የመናገር ስጦታ ያለው ሰው ሰውን ለማነጽና፣ ለመም ከር፣ ለማጽናናት ነው የሚናገረው።

''ትንቢትን የሚናገር ግን ለማነጽና ለመምከር ለማጽናናትም ለሰው ይናገራል። በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ማኅበሩን ያንጻል።''1ቆሮ14 :3

➛ትንቢት ከመጽሐፍ ቅዱስ ስልጣን ያነሰ ነው።  ሁላችንም ከመጽሐፍ ቅዱስ በታች ነን፣መጽሐፍ ቅዱስ ይገዛናል እንጂ አንገዛውም፣ይመራናል እንጂ አንመራውም፣ የምንናገረው ትንቢት በመጽሐፍ ቅዱስ ይመረመራል፣የማይመረመር ትንቢት የለም፣

2) ልሳን መናገር 1ቆሮ 12:10

በልሳን መናገር ሲባል አንድ አማኝ በማያውቀው ቋንቋ ሲናገር ማለት ነው።
በልሳን መናገር መንፈሳዊ ስጦታ እንጂ በልምምድና በጥናት፣በሂደት የሚመጣ ቋንቋ አይደለም።

➛ይህ ልሳን(ቋንቋ)ምናልባት ምድራዊ ቋንቋ አሊያም ከእግዚአብሔር ጋር በምስጢር የምንነጋገርበት ቋንቋ ሊሆን ይችላል።

ሦስት አይነት ልሳን አለ:--

ሀ) መንፈስ ቅዱስ ሰዎችን በወንጌል እንድንደርስ ሲፈልግ የሰዎቹን ቋንቋ ይሰጠናል። አንድ አማርኛ ተናጋሪ ለፈረንሳይኛ ተናጋሪ ወንጌል መመስ ከር ያለበት በሚሰማው ቋንቋ ስለሆነ ጌታ ፈረንሳይኛ ቋንቋ ሊሰጠው ይችላል። በሐዋርያት ስራ ምዕራፍ ሁለት ውስጥ የተከሰተው ይህ ነው።እነ ጴጥሮስ በማያቁት ቋንቋ ተናግረው  3000ነፍሳትን ወደ ጌታ እንዲመጡ አድርገዋል።

ለ)  ከእግ ዚአብሔር ጋር ምስጢር የምናወራበት፣የምንታነፅበት አይነት ልሳን ነው።ይህ ልሳን በአሁን ጊዜ በቤተክርስቲያን ውስጥ በስፋት እየተነገረ ያለ ነው።ይህ ልሳን የምድራዊ ቋንቋ አይደለም።መንፈሳዊ ቋንቋ ነው። ይህ ስጦታ ለሌሎች ወንጌል ለመመስከር የሚሰጥ ሳይሆን ራስን ለማነፅ እና ለእግዚአ ብሔር ምስጢር ለመናገር የሚሰጥ ነው።

በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ የሚያስተውለው የለምና፥ በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል፤
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14 : 2

በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ማኅበሩን ያንጻል። (1ኛ ቆሮንቶስ 14፡4).

ሐ) የመላእክት ልሳን

በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። 1ቆሮ 13:1
➛የመላእክት ልሳን የመላእክት ቋንቋ ነው። ሐዋርያ ጳውሎስ የመላእክት ልሳን በአማኞች ሊነገር እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል። ሆኖም ግን የተብራራ ነገር ስለሌለ መጽሐፉ እስከተናገረው ድረስ ተናግረን ዝም ማለቱ መልካም ነው።

3) ልሳንን መተርጎም 1ቆሮ12:10

➛እንደ ቃሉ መሰረት የማይተረጎም ልሳን ለሰሚው ግልፅ አይሆንም።ስለዚህ የግድ ሰዎች መረዳት በሚችሉት ቋንቋ መተርጎም አለበት።
አንድ ሰው በጉባኤ ውስጥ በልሳን ሲፀልይ ሌላው አማኝ ስለማይረዳ ልሳን የመተርጎም ፀጋ ያለው አማኝ ምን እንዳለ ሊገልጥ ይችላል።
➛ልሳን መተርጎም ያለበት ጉባኤውን ከማነፅ አንፃር ነው።አንድ አማኝ ልሳኑ ለሌሎች በረከት የሚሆነው የሚሰማው ሰው ሲረዳው ብቻ ነው።

➛ጳውሎስ በማይተረጎም ልሳን ጉባኤ ውስጥ ከመፀለይ ይልቅ ሰዎች በሚግባ ቡበት የአይምሮ ቋንቋ እንዲፀልዩ ይመክራል።ነገር ግን ሌሎችን ደግሞ አስተምር ዘንድ በማኅበር እልፍ ቃላት በልሳን ከመናገር ይልቅ አምስት ቃላት በአእምሮዬ ልናገር እወዳለሁ።1ኛ ቆሮ14 : 19

➛ልሳን የመናገር ስጦታ ያለው ክርስቲያን በተጨማሪም የሚናገረውን በምድራዊ ቋንቋ ለሰው እንዲተረጉም ሊፀልይ ይገባል።

ስለዚህ በልሳን የሚናገር እንዲተረጉም ይጸልይ።1ቆሮ14 : 13

ክፍል 97 ይቀጥላል

መሳይ አለማየሁ (ነቢይ)

💐share 💐share 💐share

@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
❤10👏1🙏1
May 23, 2026 2.4K 9