#ፍናና 10 ወለደች ማለት የተሳካላት ሴት ሆነች ማለት አደለምና በስኬት ሁሉ #አትቅና። ሃጥዕ ስንዝር ቆፍሮ ውሃ ቢፈልቅለት ከእንስሳቱ በወደቀው እዳሪ ውስጥ ያለው እህል ሳይኮተኩተውና ውሃ ሳይጠጣው የሚያሳድግለት መሬት ቢኖረው ኪዳን የለውምና ነፍሱ አትረካም።
#ልምላሜ ከነዓንን አጽድቆ በቃዴስ በረሃ ያለውን የኪዳኑን ህዝብ አይኮንነውም ስኬት አማሌቅን ቅዱስ አድርጎ ይሹሩንን አያረክሰውም።የባለኪዳኑ ህዝብ ድሉ ከአምላኩ ፈገግታ ጋር ነውና።
ጸልየህ በተሳካልህም በተበላሸብህም ነገር ኩራ በሃጥዕ ስኬት ከቀናህ መንገዱንም ትደፍረዋለህና የልብህን ምኞት ጠብቅ። ለጥቂት ግዜ ብቻ ብለህ በሃጥያት መንገድ አትሂድ የእባብ ትንሽ የለውምና።
Telegram
Forwarded fromYabinas♠️
Telegram
S H E K A Y I N A H
ይህ #የሸካይና ፔጅ ነው የዚህ አገልግሎት አላማ #ትውልዱን ወደ ተገለጠው የእግዚአብሔር ክብር እለት ተዕለት እንድትጠጋ ማገዝ ነው:: ይህ ቻናል የተከፈተው
የእግዚአብሔርን_ክብር ለተጠሙ ተሀድሶ ለሚሹ አማኞች ነው። @Shekayinaah @Shekayina_bot

18
2May 11, 2026 2.7K 14