በክርስቶስ IN CHRIST ክፍል 95 ተአምራትን የማድረግ ስጦታ (1ቆሮ.12፡9 2፡9) ➛በመጽሐፍ ቅዱስ… — #KALTUBE — TG.ME

በክርስቶስ IN CHRIST
ክፍል 95

ተአምራትን የማድረግ ስጦታ (1ቆሮ.12፡9 2፡9)

➛በመጽሐፍ ቅዱስ (በብሉይ እና በአዲስ ኪዳን) መጽሐፍት ውስጥ በጥቂቱ ከ250-265 ተአምራት ተጠቅሰዋል።

በብሉይ ኪዳን ከተጠቀሱት ዋና ዋና ተአምራቶች መካከል፡- ዘፍጥረት(ፍጥረታት) ፣ የጥፋት ውሃ ፣ የግብጽ መቅሰፍታዊ ተአምራት ጨምሮ ከ100 በላይ ልዩ ተአምራትን ይዟል።

አዲስ ኪዳን- ከ80 በላይ ተአምራትን ይዟል፣ ብዙዎቹ በጌታችን በኢየሱስ ታላላቅ  አገልግሎቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው።
ከዚህ ውስጥ የኢየሱስ ተአምራት በወንጌላት ውስጥ  ከ37–50 ያህል ተአምራት ተጠቅሰዋል። ይህ ሲባል ግን ኢየሱስ የሰራቸው ተአምራት እነዚህ ብቻ ነው ማለት አይደለም።

ኢየሱስም ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸውም ይመስለኛል። ዮሐ 21:25

➛ተአምር ማለት እግዚአብሔር የሚሰራው ከሰው አቅምና ከሰው ሃሳብ በላይ የሆነ ስራ ማለት ነው።ተአምራት  እግዚአብሔር የሚሰራቸው  ስሙን የሚያስከብሩ ስራዎች ናቸው።መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተአምራት መካከል በጥቂቱ  ባህር መክፈል፣የተዘጋ ማህፀን መክፈት፣የሞተን ማስነሳት፣
ከባዶ ነገር አንዳች ነገር ማድረግ፣ የሌለን ማምጣት፣የተጎመደ እጅ መቀጠል፣የማያዩ አይኖችን መክፈት፣መስማት የማይችል ጆሮ መክፈት፣ሁለቱን አሳና አምስቱን እንጀራ ለአምስት ሺህ ህዝብ ማብላት እና ሌሎችም እልፍ ተአምራት  መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኛለን።

➛ተአምራት የራሳቸው ባህሪና አካሄድ አላቸው።ተአምራት ለሰዋዊ ማንነታችን እንግዳ ሁልጊዜ እንግዳ ናቸው። ለአዕምራችን የማይገባንና በሳይንስ የማይረጋ ገጥ የመለየኮታዊ ጣልቃ ገብነት ውጤት ነው።

➛ተአምራት እንዴት?በሚል ጥያቄ የማይ መለሱ ነገር በእምነት የምናስተውላቸው አስደናቂ የጌታ ስራዎች ናቸው።

➛መንፈስ ቅዱስ ይህን ስጦታ የሰጠው ሁሉን ቻይነቱን ሊያሳይ ነው፤ በሁሉን ቻይነቱ በእርሱ የሚያምኑትን ለማነፅ እና ወንጌል ሲሰበክ ቃሉን ሊያፀና ነው።ሃሌሉያ!!

➛ተአምራት የመስራት ስጦታ ያለው አማኝ በእግዚአብሔር ምሪት፣ ለእግዚአብሔር ክብር፣ለብዙዎች መታነፅ ሊያውለው ይገባል።

➛ይህ ስጦታ ከጥንት ከብሉይ ኪዳን ዘመን ጀምሮ የነበረ ስጦታ ሲሆን ይህን ስጦታ የተቀበሉ ቅዱሳን ሰዎች ብዙ ተቃውሞ ደርሶባቸዋል፣ዛሬም ይደርስባቸዋል።

➛ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ የሚሰራቸውን ተአምራቶቹን የሚያናንቁ  ፈሪሳዊያን፣ ሰዱቃውያን፣ፀሐፍት እና ብዙ ሰዎች ነበሩ።ተአምራት ከተፈጥሮ አቅም በላይ የሆኑ የሰው ልጅ ችግሮችን የሚፈታ የጌታ መፍተሔ በመሆኑ በቀላሉ መረዳት ስለማይቻል። እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ተአምራትንና አስማትን ነጥሎ ባለማወቅ እውነተኛ የሆነውን ተአምራት ወደ መካድና ወደ መገሰጽ የሚሄዱ ጥቂቶች አይደሉም።

➛በዚህም ዘመን ያለን ክርስቲያኖች የሃገር መሪዎች የማይችሉት፣ሳይንቲስቶች የማይፈቱት፣የምህንድስና ጥበብ የማይፈታው፣ሳይኮሎጂስቶች የማይፈቱት፣ ቴክኖሎጂ የማይፈታው ብዙ ችግር ባለበት አለም ላይ ነው ያለነው።
➛የአለም ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ፣ ሁኔታዎች ተለወጡ ሲባል ከድጥ ወደ ማጡ የሆነበት ጊዜ ላይ ነች።በዚህ ጊዜ እጃችንን ወደ ሰማይ ዘርግተን የእግዚአብሔርን ተአምራት ልንጠብቅ ያስፈልጋል።ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንት፣ዛሬ እስከ ለዘላለም ያው ነው።ትናንት የሰራውን ተአምራት ዛሬም ይሰራናል።የኛ ድርሻ ለእኛ  የማይቻል ለእግዚአብሔር እንደሚቻል ማመን ብቻ ነው።

➛ተአምራት የመስራት ስጦታ ያለው ክርስቲያን በአሁን ዘመን በቤተክ ርስቲያን ውስጥ እምብዛም ትኩረት እየተሰጠው አይደለም።ይህ ስጦታ በሃገራችን በኢትዮጵያ ላለፉት 50አመታት እውን ሆኖ ቆይቷል የሞተ ያስነሱ አባቶችና የእግዚአብሔር ሰዎች አሉ፣መንገድ ላይ እየሄዱ የመኪና ነዳጅ አልቆባ ቸው ውሃ ላይ ፀልየው ወደ ነዳጅ ቀይረው ጉዟቸውን የቀጠሉ አገልጋዮች አሉ፣ ከቤት እንስሳት ላይ አጋንንት ያስወጡ፣ አይነስውራን፣ መስማት የማይችሉ  ላይ እጅ ጭነው ተአምር ያደረጉ አሁንም እያደረጉ ያሉ አገልጋዮች አሉ።

➛ቤተክርስቲያን ለተአምራት ስጦታዎች በሰጠችው ዋጋና ትኩረት ልክ ተአምራት ታያለች። ትኩረት የማትሰጥ ቤተክርስቲያን ተአምራት የሚለው የጥንት ክስተት እና የሰው ስም ብቻ ይሆንባታል።

➛በሚያሳዝን ሁኔታ በትምህርታቸው እና በአስተምህሯዋቸው ተአምራት የለም እያሉ የሚናገሩ ደፋር ሰዎችን በቤተክርስቲያን ውስጥ ማየት የተለመደ ሆኗል። የነዚህ ሰዎች ትልቁ ችግራቸው ተአምራት አቁሟል ሲሉ እግዚአብሔር ስራ አቁሟል እያሉ እንደሆነ አለማወቃቸው ነው።

➛ተአምራት የእግዚአብሔር የሁልጊዜ የህይወት ዘይቤው ነው።ጌታ ትናንሽ ነገር ሰርቶ አያቅም ሁሌ ተአምር ማድረግ ይወዳል። ኢየሱስ ዛሬም ያው ነው። በማንነቱ፣በስራው፣ በአላማው አልተቀየረም።
ዛሬም ኢየሱስ በስራ ላይ ነው።

ተአምራትን በተመለከተ ልንረዳ የሚገቡ እውነታዎች

◆ተአምራት ከእግዚአብሔር ስለመሆናቸው በቃሉና በመንፈስ መፈተን አለብን።
◆ እውነተኛውን ተአምራት በፍሬው መመዘን።
(አማኞችን ያንፃል?፣ ያላመኑትን ወደ ወንጌል እውነት ይጠራልን ብሎ መመዘን ይቻላል)

◆ተአምራት ሲሆን አላማውን መረዳት። ሰማያዊ የሆነ አላማና ዒላማ የሌለው ተአምራት አስማት ነው።
◆ ተአምራት ቃሉን ለማፅናት የሚውል እንጂ ለታይታ እና ለስጋዊ ጥቅም የሚውል ስጦታ አይደለም።
◆ስለ ተአምራት ጥልቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባህርያትን ማንበብና መረዳት የእያንዳንዱ አማኝ ድርሻ ነው።

◆ተአምራት እውነተኛ፣ትክክለኛ እና የሚረጋገጡ ናቸው። አየር ላይ ያለ የማይጨበጥ ፣የማይጠቅም፣ሰላቢና ውጤት አልባ ተአምራት መተት እንጂ ተአምራት አይደለም።

ክፍል 96 ይቀጥላል

መሳይ አለማየሁ (ነቢይ)

💐share 💐share 💐share

@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
❤4👍1
May 1, 2026 2.4K 4