በክርስቶስ IN CHRIST ክፍል 94 የመፈወስ ስጦታ (1ቆሮ.12፡9) ➛የፈውስ ስጦታ ሌላኛው የፀጋ ስጦታ… — #KALTUBE — TG.ME

በክርስቶስ IN CHRIST
ክፍል 94

  የመፈወስ  ስጦታ (1ቆሮ.12፡9)

➛የፈውስ ስጦታ ሌላኛው የፀጋ ስጦታ ሲሆን ይህ ስጦታ እንደሌሎቹ ስጦታዎች ቤተክርስቲያንን ለማነፅ ሌሎችን ለመጥቀም የሚሰጥ ነው።

➛የፈውስ ፀጋ በተለያዩ ህመምና ደዌ ውስጥ ላሉት ሁሉ እንዲውል የተሰጠ ነው።

የፈውስ ፀጋ ከፍተኛ የጌታ ኢየሱስ ምህረትና ፍቅር የሚታይበት ስጦታ ነው።

➛ጌታችን ኢየሱስ በምድር እያለ እጅግ ብዙ ሰዎች በህመምና በስቃይ ውስጥ ሆኖ ሲያያቸው ያዝንላቸውና ይፈውሳቸው ነበር።ዛሬም ጌታ በስራ ላይ ነው። ይህ ስጦታ ያለው አማኝ የተቀበለውን ስጦታ በነፃ መስጠት አለበት።ፈውስን በምንም አይነት መንገድ ወደ ገንዘብ መቀየር ሃጢያት ነው።

➛ጌታ በፈውስ ፀጋ የዘመኑ የህክምና ሳይንስ ያልደረሰባቸውን የጤና ችግሮች፣ የአለም የጤና ድርጅት መፍትሔ ያጣላቸውን ማንኛውንም አይነት በሽታ ፈውሷል፣ ይፈውሳል፣እየፈወሰም ነው።
የፈውስ ስጦታ በሽታ እየለየ የሚፈውስ ስጦታ አይደለም።

➛ስለሆነም ይህን ፀጋ የተቀበለ ክርስትያን ለታመሙ ሰዎች ለመድረስ ዝግጁ ሊሆንና የተቀበለውን መክሊት ሊያተርፍበት ይገባል፤ በቤተክርስቲያን ውስጥም ትኩረትና ጊዜ ሰጥቶ ለታመሙ ሰዎች መፀለይና ብዙዎ ችን በፀጋው መድረስ ይችላል።

➛ይህን ስጦታ የተቀበሉ ብዙ ሰዎች ለታመሙ ሰዎች ልዩ ሃዘኔታና ጥልቅ የፈውስ መሻት ውስጣቸው ይቀጣጠላል።የታመመ ሰው ሲያዩ ወዲያው ውስጣቸው ይቃትታል እንዲሁም እንዲፈወሱ ልዩ ፍላጎት ያድርባቸዋል።እጅ ጭነውም ይፈውሳሉ።

➛የፈውስ ስጦታ በየትኛውም አማኝ ሊሰራ ይችላል። ግዴታ የሙሉ ጊዜ አገልጋይ መሆን አይጠበቅብህም። ወይም ነቢይ ወይም መጋቢ መሆን አይጠበቅብህም። ብቻ እግዚአብሔር እንደወደደ ለልጆቹ የሚሰጠው ስጦታ ነው።
➛ይህን ስጦታ እንደተቀበልክ የምታስብ ከሆነ እና እርግጠኛ ከሆንክ በየሆስፒታሉ እየዝርክ ለታማሚዎች ፀልይ፣ቤተክርስቲያን ታመው ለሚመጡ ወገኖች ልፀልይላችሁ እያልክ እጅ ጭነህ ፀልይላቸው። አይዞህ አትፍራ!
    
➛እኔ ወንድማችሁ ይህን ስጦታ እንደተቀበልኩ ያወቅሁት ከዛሬ 14 አመት በፊት የ 9ኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ነበር። ፌሎሺፕ ላይ በሚዘጋጁ የኃይል አገልግሎቶች ለተማሪዎች በመፀለይ እንዲሁም ከትምህርት ሰአት ውጪ በየቤት ህብረቱ እየተጋበዝኩ በፈውስ ፀጋ ማገልገል ጀመርኩ። ከዛ አገልግሎቴን በቦሌ መድኃኔዓለም ሃይስኩል የተማሪዎች ፌሎሺፕ በስፋት ወደ ማገልገል መጣሁ። ከዛ ዩኒቨርሲቲ ስገባ ፌሎሺፕ ላይ ትላልቅ የፈውስ ኮንፈረንሶችን በማዘጋጀት ለብዙ ሰዎች እንፀልይ ነበር። ከትምህርት አለም በኋላ ደግሞ ገርጂ በሚገኘው ኮርያ ሆስፒታል ውስጥ የሙሉ ጊዜ አገልጋይ በመሆን ለታማሚዎች በየቀኑ እየፀለይኩ በየቀኑ የጌታን ምህረት አይቻለሁ።ጌታ ዛሬም በኔ አልፎ እየፈወሰ ነው። ምክንያቱም ይህን ፀጋ እውቅና ሰጥቼዋለው።

➛በተማሪዎች ፌሎሺፕ የተጀመረው ይህ የፈውስ አገልግሎት ሰዎች ከ HIV ከካንሰር፣ከኩላሊት ህመም፣ ከእብደት፣ ከልብ ህመም፣ ከነርቭ በሽታ፣ ሲፈወሱ አይቻለሁ። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።

➛የተቀበላችሁትን ፀጋ ማንም እንዲዪናንቅ አትፍቀዱ እግዚአብሔር በብርቱዎች ሳይሆን በደካሞች ነው የሚሰራው። ጌታ በጥጋበኞችና በትዕቢተኞች ሳይሆን እሱን ለማገልገል ፍላጎት ባላቸው ልጆቹ ብቻ ነው። ስለሆነም ይህን ፀጋ እውቅና ልትሰጥ ይገባል። አትቀልድ!!

ክፍል 95 ይቀጥላል

መሳይ አለማየሁ (ነቢይ)

💐share 💐share 💐share

@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
❤6🙏4
April 27, 2026 2.6K 1 7