በክርስቶስ IN CHRIST ክፍል 93 የእምነት ስጦታ ለአንዱም በዚያው መንፈስ እምነት፥ ለአንዱም በአንዱ… — #KALTUBE — TG.ME

በክርስቶስ IN CHRIST
ክፍል 93

 የእምነት ስጦታ

ለአንዱም በዚያው መንፈስ እምነት፥ ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ስጦታ፥ ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ፥

➛የእምነት ስጦታ አንዱ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ሲሆን ይህም አማኞች በእግዚአብሔር ላይ
 ከፍተኛ መተማመን እና የማይናወጥ ጠንካራ እምነት እንዲሁም ከልክ በላይ የሆነ መተማመን እንዲኖራቸው የሚያስችል (Extraordinary Faith ) ስጦታ ነው። ይህ ስጦታ ለቤተክርስቲያን ህንፀት (መታነፅ) የተሰጠ ስጦታ ነው።

➛ይህን ስጦታ የተቀበለው አማኝ ጉባኤው እንዲታነፅ በተቀበለው እምነት የእምነት ፀሎት ሊፀልይ ይችላል እንዲሁም በሰው አቅም የማይታለፉ ትላልቅ ችግሮችን በእምነት ድል በማድረግ ችግርን ለምስክርነት ሊቀይር ይችላል። ይህን ስጦታ የተቀበለው ክርስቲያን የእግዚአብሔርን ታላቅነት ያሳያል።በጌታ ላይ ያለው መተማመኑ ፍሬ ስለሚያፈራ እግዚአብሔርን ማመን ያለውን ተግባራዊ እውነታ ለሌሎች ያስተምራል ።ሰዎችም ይታነፃሉ፤በእግዚአብሔርም ይታመናሉ።

➛ለዚህ ስጦታ ጥሩ ምሳሌዎች ዕብራውያን 11 ላይ የተጠቀሱትን የእምነት አርበኞች ናቸው። እነዚህ አባቶች በእምነታቸው የሰሯቸውን ትላልቅና አስገራሚ ስራዎች እንዲ ሁም በጌታ ላይ የነበራቸው መተማመን ያመጣውን ውጤት በሙላት ያሳዩን የእምነት ሰዎች ናቸው።እነሱም አቤል፣ሄኖክ፣ኖኀ፣አብርሃም፣ሳራ፣ይስሐቅ ፣ያዕቆብ ፣ዮሴፍ ፣ሙሴ፣ረዓብ፣
ዳንኤል፣ኤሊያስ ሌሎችም ብዙ አባቶቻችን ነበሩ።
➛ይህ ስጦታ ልዩ የእምነት ስጦታ ነው ሁሉም ክርስቲያን ይህ እምነት የለውም። ይህ ስጦታ የጋራ እምነት ሳይሆን መንፈስቅዱስ እንደወደደ ለእያንዳንዱ እያካፈለ የሚሰጠው ስጦታ ነው።ይህ ስጦታ ያለው ክርስቲያን በሚናገረውና በሚያደርገው ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ታላቅ እጅ ይገለጣል።ይህ ስጦታ ዛሬም በቤተክርስቲያን ውስጥ ይሰራል።

           ክፍል 94 ይቀጥላል

መሳይ አለማየሁ (ነቢይ)

💐share 💐share 💐share

@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
🙏5❤2
April 27, 2026 2.1K 2 8