የኤርትራው የተቃዋሚ እንቅስቃሴ ብርጌድ ንሓመዱ፣ ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ አባላቶቹ ወታደራዊ ስልጠና… — አንድ እርምጃ — TG.ME

የኤርትራው የተቃዋሚ እንቅስቃሴ ብርጌድ ንሓመዱ፣ ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ አባላቶቹ ወታደራዊ ስልጠና መስጠት መጀመሩ ተሰምቷል። እንቅስቃሴውን የሚመሩት ግለሰቦች በአዲስአበባ ፅህፈት ቤት መክፈታቸው የተሰማው ከጥቂት በፊት ወራት ነበር።

በዐቢይ አህመድ መንግሥት እንደሚደገፍ የሚነገርለት ይህ ቡድን፣ በየካቲት፣ 2017 ዓ.ም በአዲስአበባ የከፈተውን ቢሮ “ለወታደራዊ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤትነት የመጠቀም ዕቅድ እንዳለው” ባሳለፍነው ሚያዚያ ወር ለቢቢሲ አማርኛ ገልፆ ነበር።

ብርጌድ ንሓመዱ በቅርቡ በኢትዮጵያ በሁለት ቦታዎች ወታደራዊ ስልጠና መጀመሩን ዞብል ፖስት ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ወገኖች ሰምቷል። ቡድኑ ወታደራዊ ስልጠና የጀመረበት አንደኛው ቦታ፣ በአፋር ክልል የሚገኘው ልዩ ስሙ “መጋሊ” የተባለ ስፍራ ሲሆን፣ ሌላኛው ወታደራዊ ማሰልጠኛ ቦታ ግን ሚስጥራዊ እንዲሆን መደረጉ ተሰምቷል።
👍1
May 27, 2025 246