ይህስ ምን ይባላል! የሚሊሻና የፖሊስ አባላት የመብራት ትራንስፎርመሩን በጥይት ደብድበው እንዳፈነዱት ተሰማ! አሁን ከመሸ የደረሰን መረጃ! አፋብኃ በወሎ ላስታ አሳምነው ኮር ስር የሚገኘው ኃይሉ ከበደ ክ/ጦር ዛሬ ግንቦት 18/2017 ዓ/ም በዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን ሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ በሁለት አቅጣጫ ጥቃት ከፍቶ ከባድ ጉዳት ማድረሱን መዘገባችን ይታወቃል። ከአምደወርቅ ከተማ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ልዩ ስሟ ጭላ ተብላ በምትጠራው ከተማ እና ከሰቆጣ 35km ርቀት ላይ በምትገኘው ሀሙሲት ተብላ በምትጠራው ከተማ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ ነው የፋኖ አባላቱ ጥቃቱን የፈፀሙት። በዚህ ጥቃት ከባድ ኪሳራን ያስተናገዱት የአገዛዙ ወታደሮች፡ የፋኖ አባላቱ ኦፕሬሽኑን ፈፅመው አከባቢውን ለቀው ሲወጡ የከተማውን የመብራት ትራንስፎርመር በጥይት ደብድበው እንዲፈነዳ አድርገውታል ሲሉ የአከባቢው ነዋሪዎች በአይናቸው ያዩትን መረጃ አድርሰውናል። "የሚሊሻና የፖሊስ አባላቱ የከተማዋን መብራት ትራንስፎርመር በጥይት ደጋግመው በመምታት እንዲፈነዳ አድርገውታል" ሲሉ የገለፁት የአከባቢው ነዋሪዎች፡ በአሁን ሰዓት በከተማዋ የመብራት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል ብለዋል። የፖሊስና የሚሊሻ አባላቱ ድርጊቱን ፋኖ ነው የፈፀመው በሚል ለከተማዋ ማሕበረሰብ የተናገሩ ሲሆን፡ ትራንስፎርመሩ ከሚሊሻ አባላት በተተኮሰ ጥይት ከጥቅም ውጭ ሲደረግ በቦታው የነበሩ ሰዎች ፋኖ ነው ያፈነዳው በሚል ብቻ እንዲናገሩ ከባድ ማስጠንቀቂያ ተሰቷቸዋል ነው የተባለው። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ወሎ (ቤተ-አምሓራ) ላስታ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን አሳውቋል። ድላችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ግንቦት 18/ 2017 ዓ.ም
ይህስ ምን ይባላል! የሚሊሻና የፖሊስ አባላት የመብራት ትራንስፎርመሩን በጥይት ደብድበው እንዳፈነዱት ተሰማ!… — አንድ እርምጃ — TG.ME
May 26, 2025 211