እጅግ የሚዘገንን ለማንበብም አቅምን የሚጠይቅ የምርመራ ዘገባ እነሆ ልክ የዛሬ ዓመት በዚህ ወር በምርመራ ክፍል ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ስለተገደለው ኢሳይያስ በላይ የተሠራ የምርመራ ዘገባ ኢሳያስ በላይ ማነው ? ለስድስት አመታት ያህል በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ውስጥ ከፍተኛ የሳይበር ደኅንነት ባለሙያ ሆኖ አገልግሏል። በ2014 ዓ/ም የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና የክልሉ ሰላምና ደኅንነት የሚጠቀምበት ወታደራዊ ሬዲዮ የመለያ ኮዱ በቀላሉ ተጋላጭ ሆኖ ተገኘ። ይህንን የሬዲዮ ትስስር እንደ አዲስ ማስተሳሰር ግድም ሆነ። የወታደራዊ ሬዲዮ ትስስሮች እንዲሁ በቀላሉ የሚከወኑ አይደለም። በዘርፉ ልምድ ያላቸው አለም አቀፍ ተቋማት ተወዳድረው በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሚጠይቁበት ስራ ነው። አገርን ለከፍተኛ ወጪ የዳረገ የሬዲዮ ግንኙነት መረብ እንዲሁ በቀላሉ የይለፍ ቃሉ ተሰብሮ ሚስጥሮች የሚባክኑ ከሆነ ደግሞ ሌላ የአገራዊ ደኅንነት ስጋት ነው። ይህ ስጋት በ2014 ዓ/ም በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና የሰላም እና ደኅንነት የሬዲዮ መገናኛ ላይ በግልፅ ታየ። ችግሩ እንዴት ይቀረፍ? በሚል ኢንሳ መፍትሄ ሲያፈላልግ ኢሳያስ በላይ በተቋሙ ውስጥ ያገኘውን አለም አቀፍ ልምድ በመውሰድ የክልሉን የሬዲዮ አውታር እንደ አዲስ ለማቀናጀት ሀሳቡን አቀረበ። ኢንሳ ሰባት አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን አዋቅሮ ኢሳያስን የቡድኑ መሪ አድርጎ ወደ አማራ ክልል ሸኘው። ቡድኑን በማስተባበር የአማራ ክልልን ከወረዳ ጀምሮ እስከ ዋናው ቢሮ ድረስ ያለውን የሬዲዮ ትስስር በዘመናዊ መልኩ አቀናጅቶ ለክልሉ መንግስት በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ አስረክቧል። ኢሳያስ ዛሬ በሕይወት ባይኖርም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እና የሰላምና ደኅንነት ቢሮ እስከ ወረዳ ድረስ የሚጠቀሙበት የሬዲዮ መገናኛ መረብ በዚህ ድንቅ ወጣት የተሳሰረ ነው።
እጅግ የሚዘገንን ለማንበብም አቅምን የሚጠይቅ የምርመራ ዘገባ እነሆ ልክ የዛሬ ዓመት በዚህ ወር በምርመራ… — አንድ እርምጃ — TG.ME
May 18, 2025 171 1