ፋኖ የአባቶቹን አደራ እንዳይበላ ሊጠነቀቅ እንደሚገባው አንድ የታሪክ ምሁር ገለፁ የፋኖን የትግል እንቅስቃሴ… — አንድ እርምጃ — TG.ME

ፋኖ የአባቶቹን አደራ እንዳይበላ ሊጠነቀቅ እንደሚገባው አንድ የታሪክ ምሁር ገለፁ የፋኖን የትግል እንቅስቃሴ በቅርበት የሚከታተሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የታሪክ ምሁር እንዳሉት አባት አርበኞች እንደዛሬው የመገናኛ ቴክኖሎጅው ሳይዘምን፣ በቀላሉ ለመገናኘት ምቹ መንገድ ሳኖር፣ ዘመናዊ ትጥቅ እና ስንቅ ሳይዙ በአንድ ልብ ለአንድ አላማ ብቻ በቁርጠኝነት በመታገላቸው ውድ ህይወታቸውን ገብረው ለትውልዱ ነፃ ሀገር አስረክበዋል፣ የዛሬው ትውልድ ደግሞ የአባቶችን አደራ በመጠበቅና ፈለጋቸውን በመከተል በአንድነት ለነፃነቱ መታገል ታሪካዊ ግዴታው ነው ብለዋል። ከፋሽስት ጣሊያን ጋር የተፋለሙት ፋኖዎች ቤት ንብተታቸውን ትተው ዱር ቤቴ ያሉት ቅኝ ግዛትን በመፀየፍ ለነጭ አልገዛም፣ ባህል፣ ማንነታችንና እምነታችን አይበረዝም ብለው  በአንድነት መንፈስ  በመነሳታቸው ነው ያሉት የታሪክ ምሁሩ የዛሬዎቹ አማራንም ኢትዮጵያንም ከዘረኛ እና አንባገነን ስርአት ለማላቀቅ የሚታገሉት ፋኖዎችም የተነሱበትን አላማ ከግብ ለማድረስ እኔነትን አስወግደው ለእኛነት በአንድነትና በህብረት ለአንድ አላማ በፅናት መቆም እንደሚገባቸው ተናግረዋል። ነፍጥ አንስቶ ጫካ የገባ ሀይል ሊያሳስበው የሚገባው ነፍጥ ለማንሳት ምክንያት የሆነው ጉዳይ መልስ ማግኘቱና አለማግኘቱ እንጅ ስለሚይዘው ስልጣን አይነትና እርከን መሆን እንደሌለበት አፅንኦት ሰጥተው የተናገሩት ምሁሩ የአባት አርበኞችን ቀን ስናስብ የፋኖ ሀይሎች ቅድሚያ አንድነታቸው ላይ መስራት እንዳለባቸው ደግመው ደጋግመው እንዲያስቡበት የአባቶቻችንን የትግል አላማ ፅናት በማስታወስ እና ለሀቀኛ እና ወንድማማችነታዊ ህብረት እንዲተጉ ግፊት በማድረግና በማበረታታት ነው ሲሉ አብራርተዋል። በአጭር ጊዜ የአሁኑ ትውልድ ፋኖ ልዩነቱን አጥብቦ አንድ ጠንካራ ሀይል ሆኖ እንደሚመጣ ሙሉ እምነት እንዳላቸውም የታሪክ ምሁሩ ተናግረዋል።

May 5, 2025 213