የፖለቲካ እስረኛ መንበር አለሙ ዛሬ በአገዛዙ ፍርድ ቤት የተናገረው ያለ ፍትህ በአገዛዙ ከታገትን 2 ዓመት… — አንድ እርምጃ — TG.ME

የፖለቲካ እስረኛ መንበር አለሙ ዛሬ በአገዛዙ ፍርድ ቤት የተናገረው

ያለ ፍትህ በአገዛዙ ከታገትን 2 ዓመት አልፎናል። የተከሰስነው ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ ተንቀሳቅሳችኋል ተብለን ነው።

በሚገርም ሁኔታ ግን የዜጎችን የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት ህገ-መንግስታዊ መብት በግላጭ እየጣሰ ያለው የአገዛዙ ምልምል ካድሬ(ዐ.ህግ) ያለ ከልከይ ፍትህን ነፍጎን ለ2 ዓመት ዐግቶን አልረካ ብሎ እየቀጠለ ነው።
***
የአገዛዙ ካድሬ ዐ.ህጎች ምስክሮችን ማምጣት ያልቻልነው በሰላም መደፍረስና መንገድ ስለሚዘጋ ነው የሚል ይደሰኩራሉ። ለመሆኑ አገዛዙ ሰሞኑን አማራ ክልል ከሁሉም አካባቢ የተውጣጡ የብልፅግና ታማኝ አባላት፣ ወጣትና ሴት ሊግ የድርጅት አባሎቹን በማደናገሪያ መሳሪያው የምክክር ኮሚሽን ባህርዳር እያወያየሁ ነው በማለት አገዛዙ ልሳኔ በሚላቸው የቴሌቪዥን መስኮቶቹ ነግሮናል። አረ ለመሆኑ አገዛዙ በመቶወች የሚቆጠሩ ታማኝ አባላቱን ለድንግርግር ኮሚሽን ወደ ባህርዳር አጓጉዞ ሰብስቦ ማወያየት ከቻለ በኛ ላይ ይመሰክራሉ ብሎ ያሰለጠናቸውን ቀሪ  50 የከሚሴ ሸኔ አባላት ለምስክርነት ማቅረብ ለምን ተሳነው?

ዐቃቢ ህግ ይሄን ቀልድ የሚቀለደው፣ ፍትህን እየቀበረ ያለው፣ ችሎቱን ጭምር እየመራ ያለው፣ በዳኞች ይሁንታ ነው፣ ስለሆነም ችሎቱ ዐ.ህግን ሀይ ሊለው ይገባል? ገለልተኛ ሁኖ ይዳኘን እሱ የማይሆን ከሆነ ግን

''ዳኛውም ዝንጀሮ መፋረጃው ገደል
ከምን ላይ ተቀምጦ ይነገራል በደል፡"

የሚለውን የፋሲል ደመወዝ ዘፈን ጋብዘናችሁ ከነ አካቴው ፍርድ-ቤት የምንቀር መሆናችን ልንገልፅላችሁ እንገደዳለን!
April 10, 2025 244 1