ፋኖን ትደግፋለህ ተብሎ ቂሊንጦ ማጎሪያ ታስሮ የነበረው ግለሰብ በፍርድ ቤት 300 ሺህ መቶ ብር ዋስትና ከፍሎ… — አንድ እርምጃ — TG.ME

ፋኖን ትደግፋለህ ተብሎ ቂሊንጦ ማጎሪያ ታስሮ የነበረው ግለሰብ በፍርድ ቤት 300 ሺህ መቶ ብር ዋስትና ከፍሎ እንደወጣ መልሶ በብልጽግና ቡድን ታፈነ 

በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ  በቂሊንጦ ለአስር ወራት ያህል በእስር ላይ የቆየው ሚካኤል መላክ የተባለው ግለሰብ  አሻንጉሊት የከፍተኛው ፍርድ ቤት በ300 ሺህ ብር እንዲፈታ ወስኖ ነበር ይላሉ ቤተሰቦቹ። 

ይሁን እንጂ ተከሳሹ የተጠየቀውን የዋስትና ገንዘብ አስይዞ ዛሬ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሲፈታ በር ያልታወቁ ሰዎች  አፍነው ውሰደውታል ብለዋል።

"በር ላይ ጠብቀው በኃይል ወደ መኪናቸው ውስጥ አስገቡት" ሲሉ የነገሩን  አንድ  የቅርብ ቤተሰብ ነን ያሉ  የዐይን እማኝ አፍነው ከወሰዱት ሰዎች መሀል የተከሳሹን ክስ የያዘው ናትናኤል ስንታየሁ የተባለው ዓቃቢ ሕግ አብሮ ነበር ሲሉም  ገልፀዋል።

በተለያዩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያዎች እና በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ማረፊያ ቤቶች ብንጠይቅም አድራሻውን ልናገኝ  አልቻልንም ሲሉ አክለው ተናግረዋል።

አቶ ሚካኤል መላክ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰውን ፋኖን  በሚዲያ ታግዛለህ በሚል ከ2016 ዓ/ም ሰኔ ወር ጀምሮ ለአስር ወራት ያህል በቂሊንጦ ማጎሪያ በእስር ላይ ቆይቷል።

ቀደም ሲል በ2011 ዓ/ም አዲስ አበባን ከአዲስ አበቤ ውጭ ያለ ሰው ሊመራት አይገባም በማለት  ወጣቶችን አደራጅተሀል ቀስቅሰሀል እና ስልጠና ሰጥተሀል በሚል  ለወራት ያህል በእስር አሳልፎ ነበር።

ዘገባው የመሠረት ሚዲያ ነው።
👍1
April 10, 2025 194