ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ፤
ኢትዮጵያ አገራችን እንድትበለፅግ ሁሉም ሰው ነፃና ገለልተኛ የአስተሳሰብ ለውጥ ማድረግ አለበት።
የሰው ልጅ ሙሉ አካሉ የግሉ እንደ መሆኑ መጠን፤
አስተሳሰቡም የግሉን ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆን አለበት።
ይህ ደግሞ
መላው ኢትዮጵያውያንን የሚጠቅም እንጅ
ጎጅ ነገር አይደለም።
ለምሳሌ፣
ኢትዮጵያ ውስጥ እውቅ ባሀብቶች አሉ።
እነሱ በሚያደርጉት ሰፊ እንቅስቃሴ
በርካታ ሰዎች በዛ ውስጥ ተካትተው ኑሯቸውን ይቀጥላሉ።
አንድ ባለሀብት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በእየ ድርጅታቸው ይቀጥራሉ።
የአስተሳሰብ ለውጥ ያላደረግ ሰው ግን
መቸም ቢሆን አይለወጥም።
እንዲያውም አሁን አሁን
ለአገር ሸክም እየሆነ ያለው እንዲህ አይነቱ ሰው ነው።
አስተሳሰብ
ከምቀኝነት ነፃ የሆነ፤
ማንንም የማይጎዳ፤
እራስን መግዛት የሚችል አቋም ውስጥ መሆን፤
ለውጥ አምጭ መሆን፤
እያለ የሚቀጥል ሲሆን
ለውጥ ማድረግ ደግሞ
ለአገርም ጭምር በእጅጉ ይጠቅማል።
ሁሉም ሰው ነፀ የሆነ አስተሳሰብ ይዞ ይመጣ ዘንድ የዛሬው መልዕክታችን ነው ።
☎️ 0972569377

May 10, 2026 92