"ጊዜው የሾርት ነው" የረዘመ ነገር አይፈለግም(😳🤣) ፥ ሰዉ ከአጭር ነገር ጋር ያበደ አፍቅሮት ላይ ወድቋል❤❤ short video....short movies...short stories... short scripts ...easy way of success...short memory....short answer... scroll and scroll our hand used device videos again and again🤣🤣🤣 በቃ የሆነ ያጣጠረ ነገር ይመቸናል😭😭 ላብ ያልታከለበት business, ድካም ያልታከለበት ስኬት፥ ትጋትን ያላማከለ ሃብት friendship ራሱ ዘለግ አይልም ቋሚ ጓደኛሞች ያን ያህል የሉም....በቃ መሞካከር ፋሽን ነው.....ፍቅር፥ ትዳር፥ ጓደኝነት፥ ስራ፥ ትምህርት፥ ሃይማኖት፥ everything has its own sample time አጭር ቀሚስ፥ አጭር ግንኙነት፥ አጭር ቆይታ፥ አጫጭር ኮርስ፥ አጭር ቀጠሮ ነገረ ስራችን ቢኪኒ በቢኪኒ ሆኗል😂😂 ዝንጉነታችን ራሱ short memory ለተባለ pandemic factors አሳልፎ ሰጥቶናል ድሮ ለመጋባት ሲጠናኑ ቢያንስ ሶስት አራት ዓመት ይከርሙ ነበር አሁን ላይ በ6 ወር መጠናናት የተጋቡ ጥንዶችን በብዛት አውቃለሁ ...6 ወር እንኳን የማያልቅ የሰዉን ባህሪ ቀርቶ ስም ከነ አያት ለመጠናናት አይበቃም🤣🤣🤣 "እጥር፥ ምጥን፥ ቅጥን" የሚሰኙ ቃላቶች ተለምደዋል ባያጥር ብርቱ ጉዳይ ያለበት የሃገር መሪን ይመስል ሁሉም ይጠዳደፋል😂😂 ሌላው ይቅር የዓለም ዋንጫ በአራት ዓመት አንዴ እየመጣ እንዲህ ማጠር ነበረበት??🙄🙄 ስኬት ሳይቀር በአቋራጭ ካልሆነ አይፈለግም....የሁለት ሰዓት ርዝማኔ ያለው ስብሰባ ላይ ሰብሳቢውና ተሰብሳቢው እኩል ሲያንቀላፉ ትታዘባለህ😁😁😁 ረጅም መንገድ አይ.ነዳም.....ረጅም walk አይፈለግም......ረጅም ዕድሜ መኖር ቢፈቀድ እንኳን በlife boringness ምክንያት ሰዉ ቢያጥር አይደብረውም🙄🙄🙄 ሰዉ እምነቱ ላይም አይረዝምም...ሃይማኖቱ ላይም አይከርምም....አቋማችን ሁላ ሳይቀር በፍጥነት ይቀያየራል....በህይወታችን የማንደራደርበት pillars የሉንም፤ የመርህ ሰው አይደለንም .....flexibility የራሱ ውበት ቢኖረውም አቋመ-ቢስነት ሲታከልበት አድርባይነትን ይወልዳል። አንረጋም....አንረካም...ቶሎ ተወልደን ሳንጎረምስ እናረጃለን፤ ቶሎ ተመርቀን ሳንሰራ እንጃጃለን። ዝና ሁላ ሳይቀር ቁመት የለውም...ዕውቅናም ከአንድ ሃሙስ አይዘልም...ሃሳብ አይበረክትም... እልል የተባለላቸው አይነ-ግቡ ጥንዶች ወዲያው ይፋታሉ....የት ይደርሳሉ ተብለው የሚጠበቁ ዝግጅቶች ጳጉሜያቸው ይፈጥናል........ በጋራ ሰርተው ሽቅብ ይወነጨፋሉ የምንላቸው business partners ድርጅታቸውን ይዘጋሉ....ሰማይ ራሱ ከኛ ያደመ፥ ምድር ራሷ ከኛ ያበ'ረች ይመስል ቶሎ መሽተው ቶሎ ይነጋሉ። ቀን አይበረክትም....ሰኞ ብለህ ሐሙስ ይመጣል ያኔ በመሐል የት ነበርኩ ብለህ ከራስህ ጋር ትወዘጋገባለህ🤣🤣🤣 አሁን ሁላ ይሄን ስፅፍ እንዳይሰለቸኝ short video እያየሁ ነው የጨረስኩት🤣🤣🤣 እናንተም በአንቀፅ ከፋፍላችሁት በሳምንት ውስጥ short episode አድርጋችሁ እንደምትጨርሱት እተማመንባችኋለሁ🤙🤙 Chê Z Paulos ✍✍✍ ለወዳጅ ዘመዶ ሼር ያድርጉ!! 📌ማጋራት አይዘንጋ! JOIN ✅✅✅ 📚 @HuluBooks
ጊዜው የሾርት ነው" የረዘመ ነገር አይፈለግም(😳🤣) ፥ ሰዉ ከአጭር ነገር ጋር ያበደ አፍቅሮት ላይ… — መጽሐፍ — TG.ME
July 26, 2026 6.2K 49