ምርጥ መፅሐፍ ልጋብዛችኋ ወንጀልና ፍርድ በዶስትዬቪስኪ ========= ሚጥጢ ነጥቦች ....አየህ ያልተማረ… — መጽሐፍ — TG.ME

ምርጥ መፅሐፍ ልጋብዛችኋ ወንጀልና ፍርድ በዶስትዬቪስኪ ========= ሚጥጢ ነጥቦች ....አየህ ያልተማረ ገበሬና መሃላ ያልፈፀም መነኩሴ ብቻ ናቸው በምርመራ ላይ ሁሉንም ነገር የሚክዱት።ንቁ ሰው ግን የማይቀየሩ እና ከወንጀሉ ውጭ የሆኑ ነገሮችን በሙሉ አይክድም። .....ቀኝህ የሰጠውን ግራህ አይይ ...እብደት አካላዊ ህመም ሳይሆን የአመክንዮ(ሎጅክ) ስህተትና የአመለካከት መንሸዋረር የሚፈጥረው ችግር ነው። የለውጥ አየር ፈላጊ ነህ።ስቃይን ተቀበል።ስቃይ ጥሩ ነገር ነው።ነገር ግን ራስህን እንደ ብልጥ አትመልከት።ከፊትህ ያለው ጎርፍ ከወንዝ ዳር ይተፋሃል። ሽንገላ ጠቃሚ ሃይል መሆኑ ይታወቃል።በዚች አለም እውነትን ከመናገር የበለጠ ከባድ ነገር እንደሌለ ሁሉ ከሽንገላ የቀለለ ነገር **የለም።ከምትናገረው እውነት ውስጥ አንድት ሃሰት ብትገኝ ለፀብ ትዳርግሃለች። ሙሉ በሙሉ ሀሰተኛ የሽንገላ ቃላት በአንፃሩ የሚያስማማና በእርካታ** የሚደመጥ መሆኑ ሃቅ ነው።በሽንገላ የሚገኘው እርካታ ቢጎረብጥህም ያው እርካታ ነው።የሚጎረብጥ ሽንገላ እንኳን ቢሆን ግማሹ ለአድማጩ እውነት ይመስለዋል። እኔና ሚስቴ ለስነ-ፅሁፍ ትልቅ ክብር አለን።አንድ ሰው ጨዋ መሆኑ በቂ ነው።የቀረውን ነገር በክህሎት፣በትምህርትና በጉብዝናው ሊያገኝ ይችላል።የክብር ኮፍያ ምን ያደርግለታል? ኮፍያን እንደ ዳቦ በቀላሉ መግዛት እችላለሁ።ባይሆን ኮፍያው የሚሸፍነውን ጭንቅላት ግን ልገዛው አልችልም...... ...አንብቡት......

March 22, 2026 7.7K 10